Visit Wolaita

Visit Wolaita Cultural and Historical Adventure ❤💛🖤

የዚህ ትውልድ በመሆናችን ኩራት ተሰምቶኛል 💪💪
10/12/2025

የዚህ ትውልድ በመሆናችን ኩራት ተሰምቶኛል 💪💪

የUNESCO መገለጫ | እንኳን ደስ አላችሁ መላው ኢትዮጵያዊያን እና ወላይታዎች!Gifaataa is now officially the world heritage. It is a cultural festi...
10/12/2025

የUNESCO መገለጫ | እንኳን ደስ አላችሁ መላው ኢትዮጵያዊያን እና ወላይታዎች!
Gifaataa is now officially the world heritage. It is a cultural festival celebrated by the Wolayta people in the Southern Region of Ethiopia. The festival is celebrated wearing Dinguza traditional customs. Gifaataa means, "the beginning," and is also considered the bridge from old to new, dark to light.

ጊፋታ በይፋ የአለም ቅርፅ ሆኖ ተመዘገበ። ጊፋታ በደቡብ ኢትዮጵያ በወላይታ ህዝብ ዘንድ የሚከበር ባህላዊ ፌስቲቫል ነው። ይህ ፌስቲባል የሚከበረው ባህላዊ አለባበስ ድንጉዛን በመልበስ ነው። ጊፋታ ማለት “ታላቅ” ማለት ነው ፤ እንዲሁም ከአሮጌው ወደ አዲሱ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገሪያ ድልድይ ነው!

UNESCO , New Delhi , India

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👏
በሕንድ፣ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዩኔስኮ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ጥበቃ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ያቀረበችው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" በሰው ልጅ የማይዳሰሱ የባሕል ቅርሶች ዝርዝር ስር ተመዝግቧል።

 #የሶዶ  #ከተማ  #21  #ማዞሪያ  #ማሪያም  #ቤትክርስያን  #ለልማት  #ማነቆ መሆኑ ተገለፀ ! የሶዶ ከተማ 21 ማዞሪያ ማሪያም ቤትክርስያን  ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ ያለው መንገድ...
22/11/2025

#የሶዶ #ከተማ #21 #ማዞሪያ #ማሪያም #ቤትክርስያን #ለልማት #ማነቆ መሆኑ ተገለፀ !

የሶዶ ከተማ 21 ማዞሪያ ማሪያም ቤትክርስያን ከሌዊ እስከ ግብርና ኮሌጅ ያለው መንገድ በፍጥነት እንዳይሰራ ማነቆ መሆኑን የመንገድ አስተባባሪዎች ገለፁ!

የሶዶ ሃዋርያት ቤትክርስትያን እና ለማሪያም ቤትክርስያን ከአንድ አመት በፊት አጣሪ እንዲያነሱ ደብዳቤ መሰጠቱ ይታወቃል! ይሁን እንጅ ሃዋርያት ቤትክርስትያን በሰዓቱ አጥሩን ቢያነሳም ግን ማሪያም ቤትክርስያን እስካሁን ድረስ አለመነሳቱ ለልማት ማነቆ መሆኑ ተገልጿል!

ከዚህ በፊት ለልማት አዲስ አበባ ላይ አንዋር መስግድ ቦሌ መዳነአለም ቤትክርስትያን ስፈርስ አይተናል! እንዲሁም አዳማ ድሬዳዋ ባህርዳር ከተማዎች ለልማት ስተባበሩት አይተናል!

ሶዶ ላይ ማሪያም ቤትክርስትያ ውስጥ ግን አንድ አንድ ሰርግ ገቦች ጽንፈኞች አመጽ ለማስነሳት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያየን ስለሆነ አደብ ብትገዙ ጥሩ ነው!

ማሪያም ቤትክርስያን ፊት ለፊት ላይ መነገድ ብሰራ ኮሪደር ብገባ ለቤትክርስያን ውቤት ነው እንጂ ቤትክርስያንን ለማጥፋት አይደለም!

ስለዚህ የቤትክርስያን አስተባባሪዎች ተባብራችሁ አጥሩን እንዲታነሱ በአክብሮት እንጠይቃለን ።🙏🙏🙏

Visit Wolaita
01/11/2025

Visit Wolaita

ዮ ዮ ጊፋታ!! Yoo yoo gifaata !!ዮዮ ..."ጊፋታ"  .....የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ሲሆን "ጊፋታ" ማለት ባይራ ወይም ታላቅ፣ መጀመሪያ እንደማለት ሲሆን ...
12/09/2025

ዮ ዮ ጊፋታ!! Yoo yoo gifaata !!

ዮዮ ..."ጊፋታ" .....የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ሲሆን "ጊፋታ" ማለት ባይራ ወይም ታላቅ፣ መጀመሪያ እንደማለት ሲሆን በሌላ በኩል "ጊፋታ" ማለት መሻገር (መሸጋገሪያ) ማለት ነው::

ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል::

የወላይታ ብሔር የ"ጊፋታ"ን በአል ማክበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዓመቱን ሙሉ ለአስራ አንድ ወራት በስራ ካሳለፉ በኋላ ለአንድ ወር ሙሉ በተለይም በዓመቱ መገባደጃ ያለውን ከባዱን የክረምት ጎርፍና ጭጋግ በማለፍ ከክረምት ጨለማ ወደ ብርሃን የተሸጋገርኩበት ነው ብለው ሲያከብሩ ለአዲሱ ዓመት በሠላም ስለ መሸጋገራቸው ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡበት ክብረ በዓል ነው "ጊፋታ"::

"ጊፋታ" በአል ለወላይታ ህዝብ፣ ለአከባቢውና ለሀገራችን የሚያበረክተው በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖማያዊ፣ ፖሊቲካዊ እና ባህላዊ ፋይዳዎች ይኖሩታል::

የ"ጊፋታ" በአል በወላይታ ማህበረሰብ ዘንድ የአብሮነት ስሜት እንዲጠናከር የሚያደርግ ሲሆን ይህም ማለት አብሮ መስራት፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጫወት፣ ኢኮኖሚዊ ችግሮችን በጋራ መወጣት፣ መተሳሰብና መረዳዳት የሚገለጽበት በዓል ነው "ጊፋታ"

"ጊፋታ" ሲቃረብ በሚውሉ ሶስት ዋና ዋና ገበያዎች አባቶች በአመቱ ውስጥ ያደለቧቸውን በሬዎችን በመሸጥ ኢኮኖማያዊ ጥቅም የሚያገኝበት፣ እናቶች የቅቤ እቁብ ገብተው ያጠራቀሙትን ቅቤ ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸውን ብቻ በማስቀረት ሌላውን በመሸጥ ለበዓሉ ዝግጅት የሚያስፈልገውን ገንዘብ የሚያገኙበት ታላቅ በዓል ነው "ጊፋታ"፡፡

ለ"ጊፋታ" በዓል ለእርድ የሚሆን በሬ ለመግዛት በቡድን አስራ ሁለት የሚሆኑ አባዎራዎች በየሳምንቱ ተቀማጭ ገንዘብ ይቆጥባሉ፣ በአሉ ሲቃረብ ከ"ጊፋታ" ገበያ በሬ መግዛት፣ ለልጆቻቸው አልባሳት፣ ለበአሉ ድምቀት የሚውሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ መግዛትና ማሳደስ የአባቶች ተግባር ሲሆን ለ"ጊፋታ" በአል የሚፋቅ እንሰት ከጓሯቸው መርጦ ማሳየት ተግባር በአባቶች ይከናወናል::

ለ"ጊፋታ" በዓል እናቶች በግልና በቡድን በመሆን ቅቤ ያጠራቅማሉ፣ በአባዎራ ተለይቶ የተሰጠውን እንሰት ፍቆ ቆጮ በአይነት ያዘጋጃሉ፣ የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ፣ ሴት ልጃገረዶቹ የሚያጌጡ የመዋቢያ አልባሳት፣ ለእጃቸው ድምቀት እንሶስላ፣ ለደረታቸው ሎሚና ሌሎች ቁሳቁሶችን ከ"ጊፋታ" ገበያ የመሸመት ድርሻ የእናቶች ተግባር ነው::

በ"ጊፋታ" ሹዋ ዎጋ ወይም እርድ እሁድ ለሚለኮስ "ጉሊያ" ማዘጋጀት ተግባር የወጣቱ ሲሆን ከሰኔ ወር ጀምሮ ጥቅም ላይ የማይውሉ እንጨት አይነቶችን ቆርጦ እየጎተቱ ባህላዊ ዘፈን እያንጎራጎሩ በተመረጡ አድባር በእንጨቶች "ጉሊያ" ይሰራሉ ወጣቶች ለጊፋታ::

ለ"ጊፋታ" በዓል ቅድመ ዝግጅት ወጣት ሴቶች በእናቶቻቸው ጎን በመሆን ሁሉንም የቤት ስራ ሳይመርጡ የመስራት ግደታ አለባቸው፣ ምክንያቱም ሙያ ያላት ሴት ሆና ማደግ እንዳለባት ይታመናል:: ልጃገረዶች ለ"ጊፋታ" በዓል ተውቦ እና ደምቆ አደባባይ የሚወጡበት የነጻነት በአል መሆኑ ለትዳር የደረሱ ሴቶች በ"ጊፋታ ጋዜ" ጫወታ የሚተያዩበት በዓል በመሆኑ "ጊፋታ" ለሴቶች ለየት እንደሚል ይነገራል::

የ "ጊፋታ" በዓል መቃረቡን የሚያበስሩና በህዝቡ ዘንድ እጅግ የሚታወቁ በእንቅስቃሴያቸው ከወትሮ የተለዩ ገበያዎችም ያሉ ሲሆን እነሱም "ሃሬ ሀይቆ"፣ "ቦቦዶ"፣ "ጎሻ" በመባል የሚታወቁ ሲሆን የመጨረሻው ደግሞ "ቃኤ ጊያ" ይባላል::

ይቀጥላል...

Yoo Yoo Gifaataa❤💛🖤
11/09/2025

Yoo Yoo Gifaataa❤💛🖤

YOO YOO GIFAATAA ❤💛🖤
11/09/2025

YOO YOO GIFAATAA ❤💛🖤

Address

Sodo

Telephone

+251916471226

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Wolaita posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share