Uma Promotion and Events

Uma  Promotion and Events Empowering promotions, crafting unforgettable events.💝💝🎈🎈

የዛሬዉን መድረክ በስኬት አጠናቀናል።ለነገዉ እየተዘጋጀን እንገኛለን። !
27/07/2025

የዛሬዉን መድረክ በስኬት አጠናቀናል።
ለነገዉ እየተዘጋጀን እንገኛለን።

!

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ማኔጅመንት ክፍል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ በደረሰው የድንገተኛ እሳት አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ።በትናንትናው ...
27/07/2025

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ማኔጅመንት ክፍል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ በደረሰው የድንገተኛ እሳት አደጋ የተሰማውን ሀዘን ገለጸ።

በትናንትናው ዕለት 19/11/2017ዓ.ም በወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በድንገተኛ የእሳት አደጋ እጅግ አሳዛኝ መሆኑን የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤፍሬም ገ/ሥላሴ ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለው በእሳት አደጋው ጉዳት የደረሰበት ህንጻ ከአምሳ ዓመታት በፊት የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል መሥራች እና ባለቤት በሆኑት በዶ/ር ሀሮልድ አዶልፍ የተገነባ መሆኑን በማውሳት የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ከወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር ያለው ትስስር ከሥራ ግኑኝነት ያለፈ እና ታሪካዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ከእሳት አደጋው ጋር ተያይዞ በትናንትናው ዕለት 19/11/2017ዓ.ም ከኦቶና ሆስፒታል ህክምናቸውን አቋርጠው ወደ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል እንዲዛወሩ የተደረጉ ወላድ እናቶች፣ ጨቅላ ሕጻናት፣ ጎልማሶችን እና አዛውንቶችን ጨምሮ አምሳ አንድ ታካሚዎችን ሆስፒታላችን ተቀብሎ ያለምንም ክፍያ በድንገተኛ፣ የተኝቶ ሕክምና እና የጥብቅ ጥንቃቄ ክፍሎች የሕክምና አገልግሎት እየሰጣቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አደጋውን ተከትሎ ከአደጋው ሥፍራ ታካሚዎችን ወደ ሆስፒታላችን በማዛወር ሂደት እና ተቀብሎ በማስተናገድ ሂደት ፍቅር እና ርህራሄ በተሞላበትን መንገድ ከቤት ጭምር ተጠርተው በመምጣት አገልግሎት የሰጡ የሆፒታላችን የሥራ ባልደረቦች ማለትም ከበር ከጥበቃ ጀምሮ ተቀብለው ያስተናገዱትን የጥበቃ ሠራተኞች፣ የሆስፒታሉን አንቡላስ ሾፌሮች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ ሐኪሞች እና ነርሶች እንዲሁም የረዚደንሲ ሕክምና ተማሪዎች ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል በደረሰው አደጋ ምክንያት የተጎዳውን የወ/ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ወደ አገልግሎት ለመመለስ በሚደረግ ጥረት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልጸዋል።

ሁሌም ለላቀ የሕክምና አገልግሎት እንተጋለን!
አድራሻችን፦ ወ/ሶዶ ከባሕል አዳራሽ / ጉታራ በስተጀርባ እንገኛለን
ለበለጠ መረጃ: 0465511164 ይደውሉ
መረጃዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉ https://t.me/soddochristiangeneralhospital

ኡማ ፕሮሞሽን መድረኩን በድምቀት መምራት ጀምሯል።በስኬት ለማጠናቀቅ እየተጋ ይገኛል።
27/07/2025

ኡማ ፕሮሞሽን መድረኩን በድምቀት መምራት ጀምሯል።

በስኬት ለማጠናቀቅ እየተጋ ይገኛል።

በዛሬዉ እለት 2 ድንቅ መድረኮችን በስኬት የመራዉ   አሁንበዚህ ሰዓት ለነገ መድረክ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።ስላመናችሁበትን እነመሰግነለን።ደግሞ እንደሁልጊዜዉ እናኮራችኋለን።ስለሁሉም ፈጣሪ...
26/07/2025

በዛሬዉ እለት 2 ድንቅ መድረኮችን በስኬት የመራዉ አሁንበዚህ ሰዓት ለነገ መድረክ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ስላመናችሁበትን እነመሰግነለን።
ደግሞ እንደሁልጊዜዉ እናኮራችኋለን።

ስለሁሉም ፈጣሪ ይመስገን።

ተልዕኮ ለትውልድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የክረምት ወራት የበጎ ተግባር በወላይታ ሶዶ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።ወላይታ ሶዶ፦ ሐምሌ18/ 2017 ዓም ተልዕኮ ለትውልድ ...
26/07/2025

ተልዕኮ ለትውልድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የክረምት ወራት የበጎ ተግባር በወላይታ ሶዶ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

ወላይታ ሶዶ፦ ሐምሌ18/ 2017 ዓም ተልዕኮ ለትውልድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በወላይታ ሶዶ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጰጥሮስ ለማ የአርንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ የአየር ንብረት ለውጥ ችግሮችን በዘላቂነት ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

አቶ ጰጥሮስ አክለው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት በመንግስት ብቻ ሳይሆን በእምነት ተቋማት የሚደረገው ስራም ሊጠናከር እንደሚገባው አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ቪዥነሪ አብያተ ክርስቲያንት ህብረት ፕረዚዳንት እና ተልዕኮ ለትውልድ አለም አቀፍ መስራችና ባለራዕይ ሃዋሪያው ዘላለም ጌታቸው በበኩላቸው የእምነት ተቋማት ወጣቱን ትውልድ በመልካም ስነምግባር ከማነፅ በአሻገር ተፈጥሮን መጠበቅ ይገባል ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የቤተክርስቲያኒቱ አባላት በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በማካሄዳቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በቀጣይ የእንክብካቤ ስራዎችን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የእርከን ስራ ጥበብን ለዓለም ያስተዋወቀ የብርቱዎች ምድር ኮንሶየኒዉዮርክ ተፈጥሮአዊ መስህብ ባለቤት ኮንሶየኳስ ጠቢባን መገኛ ኮንሶእንኳን ደስ ያለሽእንኳን አብሮ ደስ ያለን።
26/07/2025

የእርከን ስራ ጥበብን ለዓለም ያስተዋወቀ
የብርቱዎች ምድር ኮንሶ
የኒዉዮርክ ተፈጥሮአዊ መስህብ ባለቤት ኮንሶ
የኳስ ጠቢባን መገኛ ኮንሶ

እንኳን ደስ ያለሽ
እንኳን አብሮ ደስ ያለን።

መልካም ምሽት
26/07/2025

መልካም ምሽት

በርቺ በርቺ
26/07/2025

በርቺ በርቺ

ኡማ ፕሮሞሽን በዛሬው እለት ሁለት መድረክ በብቃት መርቷል።Uma  Promotion and Events ኤግዞዳስ ፋርም ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ነው...
26/07/2025

ኡማ ፕሮሞሽን በዛሬው እለት ሁለት መድረክ በብቃት መርቷል።
Uma Promotion and Events

ኤግዞዳስ ፋርም ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ነው

ወላይታ ሶዶ ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም

ኤግዞዳስ ፋርም ኮሌጅ ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ3 መቶ 79 በላይ ተማሪዎችን በዛሬው እለት እያስመረቀ ይገኛል።

የዛሬው ተመራቂ ተማሪዎች በግብር ዘርፍ ማለትም በCrop production , በCooprative, በAnimal Health እና በNRM-Natura Resources Mgt የሰለጠኑ ናቸው።

ኮሌጁ ከመደበኛ ሥልጠና ባሻገር በተያዩ የግብርና ሙያ ዘርፎች : ሰው ሠራሽ እንስሳት ማደቀያ; ዶሮ እርባታ; የከተማ አረንጓዴ እና ውበት ስራ ; ንብ እርባታ ሰራ እየሰራ ይገኛል።

ተቋሙ በአጭር ጊዜ የሥልጠና ዕውቅና በማግኘት ስራ አጥ ወጣቶችን በማሠልጠን ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲላቀቁ ተግቶ እየሰራ ነው።

ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት ከ1ሺህ 2መቶ በላይ ለሆኑ ሠልጣኞች በአራት የግብርና ሙያ ዘርፎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

ኤግዞዳስ ፋርም ኮሌጅ ከስልጠናው ባሻገር የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከል በመሆን ከተለያዩ አከባቢዎች ለሚመጡ ተመዛኞች አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ መንግሥቱ ትግሮ;የኮሌጁ ዋና ስራ አስከያጅ ዶክተር ተሻለ አረጋው ጨምሮ፣ የወላይታ ዞን ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማቸው ከፍያለው; የኤግዞዳስ ፋርም ኮሌጅ ማኔጅሜንት አባላት; መምህራን; የተመራቂ ቤተሰቦች; የዕለቱ ተመራቂዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

26/07/2025

ኦቶና ሆስፒታል የተከሰተዉ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

ህይወታችሁን አደጋ ላይ ጥላችሁ የተረባረባችሁ ሁላችሁም ከክፉ ይሰዉራችሁ።

ኡማ ፋሚሊ
26/07/2025

ኡማ ፋሚሊ

Address

Sodo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Uma Promotion and Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Uma Promotion and Events:

Share