Sidama Buna football Event

Sidama Buna football Event About all event And the mangement in and out of bored the realtion of team with all famile of sidama buna

መልካም ዜናለ CAS ያቀረብነው አቤቱታ ደብዳቤ ተቀባይነት አግኝቶአል እንኳን ደስ አላችሁ መላው የሲዳማ ህዝብ መላው ደጋፊ!በቀጣይ የምኖረውን ህደት ለህዝቡ የምናሳውቅ ይሆናል።
14/07/2025

መልካም ዜና
ለ CAS ያቀረብነው አቤቱታ ደብዳቤ ተቀባይነት አግኝቶአል እንኳን ደስ አላችሁ መላው የሲዳማ ህዝብ መላው ደጋፊ!

በቀጣይ የምኖረውን ህደት ለህዝቡ የምናሳውቅ ይሆናል።

አታምታቱ !የተባለው ከገንዘብ አወጣጥ ስርዓት ጋር ተያይዞ ዋንጫ የተነጠቀ ክለብ የለም እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ዋንጫ ተነጥቆ የሚያውቅ ክለብ የለም አልተባለም። ወይ በደምብ አድምጡ ወይ ዝ...
13/07/2025

አታምታቱ !

የተባለው ከገንዘብ አወጣጥ ስርዓት ጋር ተያይዞ ዋንጫ የተነጠቀ ክለብ የለም እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ዋንጫ ተነጥቆ የሚያውቅ ክለብ የለም አልተባለም። ወይ በደምብ አድምጡ ወይ ዝም በሉ..

ደግሜ ላረጋግጥላችሁ በገንዘብ አወጣጥ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት እና ከቀጣዩ አመት ውድድር የሚታሰብ ነጥብ ቅነሳ እንጂ ዋንጫ የተነጠቀ ምንም አይነት የአለማችን ክለብ የለም።አንብቡ ..አድምጡ

እኛ የምናወራው ስለ እግርኳስ ህግ እና ህግ ብቻ ነው። ፓለቲካችሁን እዛው... የምታስፈራሩት አስፈራሩ እውነትን እስከያዝን የምንፈራው አንዳችም ነገር የለም።

አሳቋቸው ፣ አስፈራሯቸው እያሉ ስትራቴጅ ነድፈው የሚሰሩ የፌደሬሽን አመራሮች አያዋጧችሁም። እንኳን ለእናንተ ለራሳቸውም አይሆኑ። እድሜልካቸውን በራሳቸው ሴራ ራሳቸው እንደወደቁ ነው። ይልቅስ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፍትሀዊ አለመሆን ነገም ራሳችሁ ላይ ስለሚደርስ ከእውነት ጋር ቁሙ። አታጭበርብሩ !

✍️ አሉላ ፍሬዉ
-----------------

ስለ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፍትህ ለምታደርጉት ብርቱ ትግል በሙሉ ከልብ እናመሰግናቹሀለን። ከጎናችሁ ነን። በርቱልን!

አሁንም እንላለን :-
!
!!

Justice for Sidama Bunna FC! ⚖️🏆Confederation of African Football we call on you to uphold the values of fairness and sp...
12/07/2025

Justice for Sidama Bunna FC! ⚖️🏆

Confederation of African Football we call on you to uphold the values of fairness and sporting integrity.

Sidama Bunna FC won the 2025 Ethiopian Cup fairly and was officially awarded the trophy by the Ethiopian Football Federation (EFF). The Club relied on a valid court order and played in good faith, with no objections raised by the EFF, the opposing club, or any other body during the competition.

24 days after celebrating the title, without any new evidence or hearing, the EFF stripped our Club of the trophy—violating the principle of finality of sporting results, equality, and due process under FIFA/CAF rules.

This injustice must not stand. We urge to intervene and ensure that Sidama Bunna FC is reinstated as rightful champions and given its place in CAF competition.

Let the game be decided on the field, not reversed in closed rooms✊🏿!

‎  !!‎‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለአለም የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት Court of Arbitration for Sport (CAS) በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተወሰነበ...
11/07/2025

‎ !!

‎ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለአለም የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት Court of Arbitration for Sport (CAS) በዛሬው እለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተወሰነበትን ኢፍትሀዊ ዉሳኔ በመቃወም የይግባኝ ደብዳቤ አስገብቷል።

‎የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲዳማ ቡና ሰኔ 1/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋንጫ አሸንፎ የወሰደዉን ዋንጫ ለወላይታ ዲቻ ተመላሽ ይደረግ በማለት ሰኔ 24/2017 ዓ.ም የወሰነዉን ኢፍትሀዊ ዉሳኔ በመቃወም ክለቡ በዛሬዉ እለት ለአለም አቀፍ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት (CAS) የይግባኝ ደብዳቤ አስገብቷል።

‎ክለቡ ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቅሬታ እና የይግባኝ ደብዳቤዎችን ቢያስገባም ምላሽ ማግኘት ባለመቻሉ ወደዚህ ሂደት እንዳመራ ገልጿል።

በ‎Switzerland ሎዛን ወደ ሚገኘዉ የCourt of Arbitration for Sport (CAS) ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የይግባኝ ደብዳቤዉን ለማስገባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ የቆየ ሲሆን እንዲሁም ቅሬታ ለማስገባት የሚጠበቁ ዉስብስብ ሂደቶችን በሙሉ አልፎ በዛሬው እለት የይግባኝ ደብዳቤዉን ማስገባቱ ተረጋግጧል።

‎የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ለመላው የክለቡ ደጋፊዎች እና የስፖርት ቤተሰቡ በሙሉ ጉዳዩ የደረሰበትን ደረጃ እየተከታተለ እንደሚያሳዉቅ እየገለፀ የክለቡ ደጋፊዎች፣ የስፖርቱ አፍቃሪያንና መላው ሕዝባችን በትዕግስት እንዲጠባበቅ ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል።

 #ለእውነት የቆሙ የኢትዮጵያ ምርጥዬ ጋዜጠኞች!የስፖርት ጋዜጠኛነት ምን እንደሆነ ለአለም እያሳዩ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣የኢትዮጵያ  #እግርኳስ ፌደረሽን የወሰነው ያልተገባ ውሳኔ  ደጋፊዎችን ወደ...
11/07/2025

#ለእውነት የቆሙ የኢትዮጵያ ምርጥዬ ጋዜጠኞች!
የስፖርት ጋዜጠኛነት ምን እንደሆነ ለአለም እያሳዩ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣የኢትዮጵያ #እግርኳስ ፌደረሽን የወሰነው ያልተገባ ውሳኔ ደጋፊዎችን ወደአልተፈለገ አቅጣጫ ነገሮችን እንዲወስድ ብያደርግም እነዚህ ጋዜጠኞች ግን ለእውነት በመቆም እውነታውን ለአለም እያሰሙ ይገኛሉ።
ስማቸው:
1. Epherem Yemane
2. Fikir Yilikal
3. Girmachew Eneyew
4. Sofoniyas Eneyew

ጨወታው ፖለቲካዊ ቅርፅ እንዳይዝ እያደረጉ ያሉ የኢትዮጵያ ጋዜጤኞችን መንግስት ልሸልማቸው ይገባል!

08/07/2025
07/07/2025
የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች  #እቃወማለሁ ! በማለት ታላቅ የSocial Media ዘመቻ አስጀምረዋል💪 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነው ውሳኔ ከCAF እና FIFA ህግጋት አንጻር ግልፅ መጣ...
05/07/2025

የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች #እቃወማለሁ ! በማለት ታላቅ የSocial Media ዘመቻ አስጀምረዋል💪 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወሰነው ውሳኔ ከCAF እና FIFA ህግጋት አንጻር ግልፅ መጣረሶች ያሉት በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን !

የሊግ ካምፓኒው በ Sample 4 ክለቦችን መረመርኩ በማለት ያቀረበውን ውሳኔ ከፍትሃዊነት አንጻር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውድቅ ማድረግ ይገባው ነበር!

!
!
!

ከአውሮፓ ሲዳማ ማህበር የተሰጠ ይፋዊ መግለጫበአውሮፓ ሲዳማ ማህበር የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እኛ፣ የአውሮፓ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ...
04/07/2025

ከአውሮፓ ሲዳማ ማህበር የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ

በአውሮፓ ሲዳማ ማህበር የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ እኛ፣ የአውሮፓ የሲዳማ ተወላጆች ማህበር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ አጥብቅን እንቃወማለን።

ውሳኔው ፍትሃዊነትን የጎደለው፣ የፖለቲካ ጣልቃገብት የተሰተዋለበት፣ እንዲሁም ግልጸኝነት እና ወጥነት የጎደለው መሆኑን እኛ፣ የአውሮፓ የሲዳማ ተወላጆችን እጅጉን አሳዝኖናል።

ፌዴሬሽኑ የሁሉንም ተሳታፊ ክለቦች የፋይናንስ አስአሰራር ሳይገመግም፣ የተገመገሙ ቡድኖችን ብቻ ጥፋተኛ ማለቱ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም። ደግሞም፣ ከተገመገሙት ከአራቱ ክለቦች ሁሉም የፋይናንስ ችግር አለባቸው ማለት ሁሉም ሊጉ ክለቦች ችግር እንደሚኖርባቸው ግልጽ ማሳያ ስሆን ቅጣቱ በሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ላይ ብቻ መሆኑ ተቀባይነት የለውም። ከተገመገሙት አራቱ ክለቦች ሁለቱ የሲዳማ ክለቦች መሆናችዉም በራሱ በብሔሩ ላይ የተነጣጠረ አድሏዊ ድርግት ስለመኖሩ ጉልህ ማሳያ ነዉ።

ይህ አይነቱ አድሎአዊ አፈፃፀም መሰረተ ቢስ ከመሆኑም በላይ ተቋማዊ አድሎአዊነት ማሳያ መሆኑን እናምናለን። ሁሉም ክለቦች በተመሳሳይ መስፈርት ሊመዘኑ ሲገባ የማስተካከያ እርምጃ በከፊል ግምገማዎችና ግምቶች ላይ ተመሰርቶ የተሰጠ ውሳኔ መሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን።

በተጨማርም ፣ ፌዴሬሽኑ ከፊፋ የተላከውን ደብዳቤ በወቅቱ አለማድረስ የራሱ ጥፋት ሆኖ እያለ፣ ሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ጥፋተኛ መባል በምንም መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም። ፌዴሬሽኑ የራሱን ጥፋቶች እና የአሠራር ጉድለቶች ወደጎን በመተው ክለቡን ጥፋተኛ ለማለት የሄደበት ርቀት አለመቀበል ብቻ ሳይሆን በሕግ መጠየቅ እንዳለበት እናምናለን።

የፌዴሬሽኑ ውሳኔዎች ፍትሃዊ ካለመሆናቸውም አልፎ ተለዋዋጭ እና የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ያለበት እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ደግሞም ፌዴሬሽኑ ፕረዚዳንት እግርኳስ ሊግ ማጠናከር ሲገባው፣ በደካማ የማስተዳደር አቅም መነሻነት የመበታተን እንዳለበት በቃለምልልሱ ወቅት ምክረ ሀሳብ ማቅረቡ ፍጹም አባገነናዊንት ማሳያ እንደሆነ የሚያስታውቅ ነው።

ፌደሬሽኑ 100 ፐርሰንት የተበላሸ ፋይናንስ አስተዳድር ያለበትን ሊግ መምራት ማለት በተገቢዉ የፋይናንስ አስተዳድር ሕጎችንና ደንቦች ተግባዊ ለማድረግ የተሠሩ ሥራዎች ያለመኖራቸዉ ማሳያ ሲሆን የራስን ጥፋት ለመሸፈን ክለቡን ተጠያቂ ለማድረግ የተኽሄደበት ርቀት ተቀባይነት የለዉም።

የዋንጫ አስጣጡን ስርዓት ተከትሎ ለተባከነዉ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ንብረት እና ስነልቦና ጫና በሙሉ ፌደሬሽኑ ተጠያቂ መሆን እንዳለበት እናምናለን።

ለሲዳማ ቡና ደጋፊዎች፣ ለሲዳማ ህዝብ እንዲሁም በፍትህ፣ በርትዕና በክብር ለሚያምኑ ሁሉ ጋር አጋርነታችንን እንገልጻለን። የፌደሬሽኑ ውሳኔ በሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ላይ ብቻ የተሰነዘረ ጥቃት ሳይሆን፣ መላውን የሲዳማ ሕዝብ ክብር የነካ ነው ብለን እናምናለን።

በመሆኑም ይህንን ጉዳይ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች ለማድረስ እንገደዳለን። ፍትህ እስኪሰፍንና ሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ በእኩልነትና በክብር እስኪስተናገድ ድረስ ሰላማዊ ትግላችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እያስታወቅን በሲዳማ ቡና እግርኳስ ክለብ ላይ የተወሰነው ውሳኔ በአስቸኳይ እንዲስተካከል፣ ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን በያዘበት መንገድ ላይ ገለልተኛ ምርመራ በሁሉም ክለቦች እንዲደረግና ፋይናንስ አስተዳደር ችግሮች እንዳሉ እንደሌሉ እዲያጣራ ፌደሬሽኑ በአስችኳይ የሚከተሉ ጉዳዮች እንዲያስተካከል እንጠይቃለን።

‎የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ !!‎‎ሰኔ 1/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋንጫ ክለባችን ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2-1 በማሸነፍ ያነሳዉ...
03/07/2025

‎የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ !!

‎ሰኔ 1/2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ዋንጫ ክለባችን ሲዳማ ቡና ወላይታ ዲቻን 2-1 በማሸነፍ ያነሳዉን ዋንጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አላግባብ በሆነ መንገድ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ ይሰጥ በማለት የወሰኑትን ዉሳኔ በመቃወም የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ በዛሬው እለት የቅሬታ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብቷል።

‎የቅሬታ ደብዳቤ ለማስገባት በተቀመጠዉ ቀነ ገደብ መሰረት ክለባችን በዛሬዉ እለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አላግባብ ዋንጫው ከእኛ እንዲነጠቅ በማለት የወሰነዉን ዉሳኔ በድጋሚ እንዲያጤን እና እንዲያስተካክል በማለት የተለያዩ የFIFA እና የሀገራችን የእግር ኳስ መተዳደሪያ ደንቦችን በመጥቀስ በዉሳኔዉ ላይ ቅሬታዉን በመግለፅ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ በማለት ገልፆ ደብዳቤ አስገብቷል።

‎ክለባችን ሲዳማ ቡና የመጀመሪያ ምዕራፍ ህጋዊ ሂደቱን በተከተለ መልኩ ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ ያስገባ ሲሆን በቀጣይም ፍትህ እስኪያገኝ ድረስ ህጋዊ ሂደቶችን እየተከተለ ወደተለያዩ ምዕራፎች የሚያመራ ይሆናል።

‎ለክለባችን ፍትህ እየታገላችሁ ያላችሁ በሙሉ በርቱልን መላው የሲዳማ ቡና ደጋፊ እና የስፖርት ወዳዱ ማህበረሰባችን ከጎናችሁ ነዉ።

‎ #ፍትህለሲዳማቡና !!
‎ #ፍትህለእግር ኳስ !!

Address

Hh
Awassa
HH

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251916441477

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama Buna football Event posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sidama Buna football Event:

Share

Category