24/01/2026
በሀገር በቀሉ አይቤክስ ቴክኖሎጂ የጎለበተው ጠብታ ፈንድ www.tebitafund.org የተሰኘ አለም አቀፍ የገቢ ማሰቡሰቢያ ሶፍትዌር ቅድመ ምረቃ ተከናወነ።
በዛሬው እለት በአይቤክስ ቴክኖሎጂስ እና ፕሮሞሽን የበለጸገ ጠብታ ፈንድ www.tebitafund.org የተሰኘ ለተለያዩ ዓላማዎች በቀላል መንገድ ከየትኛውም አለም ገቢ ማሰባሰብ ወይም የፈንድ ራይዝ ማድረግ ለሚሹ ሁሉ ጎ-ፈንድሚ እና መሰል ፕላፉት ት ፎርሞችን የሚተካ እና ከ5-10 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ካምፔይን በመፍጠር ፣ ደጋፊዎቻቸው በዴቢት ክሪዲት ካርድ እንዲሁም ቴሌብር፣ ሲቢኢ ብር እና ሊሎች 10 የሃገር ውስጥ የክፍያ አማራጭን በመጠቀም ፈንድ መሰብሰብ የሚያስችል ፕላትፎርም ተመርቋል።
በምህርቃት ስነ ስራአቱ ላይ ክቡር አቶ መሃመድ አል-አሩሲ፣ ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር እና ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በመድረኩ ስለጠብታ ፈንድ አስፈላጊነት ንግግር ያደረጉት ኢንጂነር ቢጃይ «ጠብታ ፈንድ ሃሳብ ኖሯቸው በክራውድ ፈንድ አማካኝነት በቀላሉ ሌሎች በማስተባበር ቢዝነስ መጀመር እንደሚቻልበት አንስተው ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያ በማወዳደር የስራ ማስጀመሪ ፈንድ የሸለምነው እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ፕላትፎርም ባለመኖሩ» መሆኑን አንስተዋል። ፕሉትፎርሙ እጅግ ወሳኝና አንገብጋቢ ብለው የገለፁት እንጂነሩ እስከአሁን ባለመሰራቱ ጥያቄ ያጭርባቸው እንደነበር ገልፀ ለዚህ ፕላትፎርም መበልፀግ ወጣት ኢዘዲን ካሚልንና በእሳቸው ስር ያሉ ኢንጅነሮችን አመስግነዋል።
የአቤክስ ቴክኖሎጅስ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወጣት ኢዘዲን ካሚል በበኩላቸው ፕላትፎርሙ፣ ለትምህርት፣ ቤተ-እምነት ማስገንባት፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ፕሮጄክቶች በፋይናንስ እጥረት ከህልማቸው የተለዩ የሀሳብ ባለቤቶችን የፈጣራ ባለሙያዎችን ሃሳባቸውን በመሸጥ ማህበረሰቡን በማስተባበር ፈንድ እንዲያገኙ ያስችላል ብለዋል።
ፕላትፎርሙ የተቸገሩትን ከማገዝ በተጨማሪ ከአለም አቀፍ ለጋሾች ጋር የሚያገናኝ ሀገር በቀል የገቢ ማሰባሰቢያ ወይም የፈንድ ራይዝ ፕላትፎርም ሲሆን በሙከራ ሂደቱ እጅግ ውጤታማና ደህንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ይህ ፕላትፎርም ድጋፍ ማሰባሰብ ለሚሹ ተቋማት (ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች) ለስራ ፈጣሪዎችና ተማሪዎች ፤ ለህክምናና ለትምህርት እንዲሁም ለተለያዩ በጎ አላማዎች ጠብታ ፈንድን በመጠቀም በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ፈንድ ማሰባሰብ ያስችላል። www.tebitafund.org ለመጠቀም ለሚሹ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች በየትኛው ሰዓትና ቦታ ህግና ግዴታዎችን ጠብቀው መጠቀም እንደሚትችሉ አይቤክስ ቴክኖሎጂስ ጥሪውን አቅርቧል።