06/03/2020
ዕለተ አርብ የወጡ የዝውውር ወሬዎች እና ሌሎችም ዜናዎቻችንን ያንብቡ! 👉 ላይክ፣ ኮመንት እና ሼር በማድረግ ዜናዎቻችን በቅድሚያ እንዲደርሷቹ ማድረግ ትችላላችሁ!(አድዋ አድዋ አድዋ አድዋዋዋ!)
────────────────────────
▷ ማንቸስተር ዩናይትዶች በጁዴ ቤሊንግሃም ዝውውር ላይ ዶርትመንድን ለመፎካከር ተዘጋጅተዋል። ምንም እንኳን እንግሊዛዊው ባለተሰጥዎ የክንፍ መስመር ተጭዋች በክረምት ወደ ዶርመንድ ለመዛወር ተስማምቷል ቢባልም ቀያይ ሰይጣኖቹ ታዳጊውን ለማስፈረም አሁንም ተስፋ አልቆረጡም። ኢድ ውድዋርድ ዝውውሩን ለመቀማት በግል እየሰሩ ነው። (The Athletic)
────────────────────────
▷ አርሰናሎች የፌይኖርዱን ቱርካዊ ከ21 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አማካይ ተጭዋች ኦርኩን ኮኩ ለማስፈረም የ£23m ሂሳብ ሊያቀርቡ ተዘጋጅተዋል።
(Mail)
────────────────────────
▷ ማንቸስተር ሲቲዎች ለስኪኒዩር ዝውውር እስከ €85m ለማቅረብ ፍቃደኖች ሆነዋል። የኢንተር ሚላኑን መሃል ተከላካይ በክረምት ለማዛወር ከዚህ በፊት አቅርበውት የነበረው የ €65 million ሂሳብ ውድቅ ሲሆን የጣሊያኑ ክለብ ለዝውውሩ ከ€85m (£74m/$95m) በላይ ይፈልጋል። (claciomerkato)
────────────────────────
▷ የኤቨርተኑ እንግሊዛዊ የ22 አመት አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን የወደፊት ቆይታውን በቶፌሶቹ ቤት ለማድረግ ወስኗል። በክለቡ እስከ 2025 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ረዥም ኮንትራት ለመፈራረም ተቃርቧል። (Times - subscription required)
────────────────────────
▷ የማንቸስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ የቼልሲውን የ18 አመት ስኮትላንዳዊ አማካይ ቢሊ ግላመር ለማስፈረም እየተከታተለው ይገኛል። ተጭዋቹ ሊቨርፑልን በFA Cup ሲያሸንፉ የጨዋታው ኮከብ ያስባለውን እንቅስቃሴ ማሳየቱ ይታወሳል። (Eldesmarque, via Express)
────────────────────────
▷ የአርሰናሉ አለቃ ሚካኤል አርቴታ የሪያል ማድሪዱን ስፔናዊ የ23 አመት አማካይ ዳኒ ሲባሎስን በቋሚ ዝውውር ለማስፈረም ክለቡን እነጋግሯል ስለመባሉ ሃሰት ሲል አስተባብሎታል። (Marca)
────────────────────────
▷ መድፈኞቹ የጌንቱን የ20 አመት ካናዳዊ የፊት መስመር ተጭዋች ጆናታን ዴቪድን ለማስፈረም ፍላጎታቸውን ገልፀዋል። ጋቦናዊው ኢንተርናሽናል ፒርኤምሬክ ኦበምያንግ በክረምት ክለቡን ከለቀቀ በሚል ከወዲሁ ምትኩን እያዘጋጁ ነው። (Mirror)
────────────────────────
▷ የማንቸስተር ዩናይትድ ከቻይናው ሱፐር ሊግ ክለብ ሻንጋይ ሺኑዋ በውሰት ውል የፈረመው የ30 አመት ናይጄርያዊ አጥቂ ኦዲዮን ኢግሃሎን ዝውውር በቌሚነት ለመቀየር እያጤኑበት ነው። (Mail)
────────────────────────
▷ ቼልሲዎች የትራባዝፖሩን የ23 አመት ቱርካዊ ግብ ጠባቂ ኡግሪካን ካኪር የ25 አመት ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛብላጋ ምትክ አድርገው ሊያስፈርሙት ይፈልጋሉ። የተጭዋቹ ስም ከሊቨርፑል ዝውውር ጋርም ተነስቶ ሲነሳ ቆይቷል። (Fotospor, via Express)
────────────────────────
▷ የፕሪሚየር ሊጉ የሃገር በቀል ተጭዋቾች አዲስ ህግ ሊቨርፑሎች በክረምት የዝውውር መስኮት ላይ ሊያስፈርሙ እቅድ የያዟቸውን ተጭዋቾች ግዢ ላይ እክል ሊፈጥሩባቸው እንደሚችል ተገምቷል። ክለቡ ጀርመናዊውን የ24 አመት የRB Leipzig's አጥቂ ቲሞ ወርነር ዝውውር ላይ ተፅህኖ ሊፈጥርባቸው ይችላል። (Liverpool Echo)
────────────────────────
▷ እንግሊዛዊ ክንፍ ተጭዋች ጃደን ሳንቾ የቤሩሲያ ዶርትመንድን የዝውውር ጥያቄ ለመቀበል ሲል ከማንቸስተር ሲቲ ቀርቦለት የነበረውን የሳምንታዊ £30,000 ደሞዝ ኮንትራት ውድቅ በማድረግ ወደ ጀርመን አቅንቷል። (Mail)
────────────────────────
▷ ቶተንሃሞች እንግሊዛዊውን የ19 አመት አማካይ ኦሊቨር ስኪፕ አዲስ ኮንትራት ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። (Football Insider)
────────────────────────
▷ ፒኤስዤዎች ለኬይላን ምባፔ አዲስ ኮንትራት በማቅረብ ከኔይማር የላቀ አመታዊ ረብጣ ደሞዝ ሊከፍሉት ፍቃደኞች ሆነዋል። ሪያል ማድሪድን ጨምሮ የአውሮፓ ትልልቅ ክለቦች ሊያስኮበልሉት ወኪሎችን ሲያነጋግሩ ቆይተዋል። የተጭዋቹ ኮንትራት በ2022 የሚጠናቀቅ ይሆናል። (Paris Unitde)
────────────────────────
▷ አርሰናል እና ኤቨርተኖች የናፖሊውን የ32 አመት ቤልጂየማዊ አጥቂ ድሬስ መርተንስን ለማስገረም ቀርቦላቸው የነበረውን እድል አምክነዋል። ተጭዋቹ ባለፈው ጃንዋሪ 10 ላይ ለውጭ ክለቦች በነፃ ዝውውር መልቀቅ እንደሚችል ኮንትራቱ ላይ ሰፍሮ ነበር። (Star)
────────────────────────
▷ ሌስተር ሲቲዎች ከ25 አመቱ የማርሴይ ፈረንሳዊ አማካይ ሞርጋን ሳንሶንን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል። (Jeunes Footeux, via Leicester Mercury)
────────────────────────
▷ ባርሴሎናዎች ስለ ፊሊፕ ኩቲንዎ የወደፊት ቆይታ ሁኔታ እያጤኑበት ይገኛሉ። የካታላኑ ክለብ በክረምት ሊያዘዋውር ካቀዳቸው ትልልቅ ዝውውሮች ስምምነት ላይ ብራዚላዊውን አማካይ እንደአማራጭነት ድርድሩ ላይ ለማቅረብ ያስባሉ። (sport)
────────────────────────
▷ ሎሪ ሳኔ ከዚህ የውድድር አመት በላይ በማንቸስተር ሲቲ ስለመቆየት እያጤነበት ይገኛል። በኢትሃድ ስቴዲየም የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም እንደሚችልም ይገመታል። ባየር ሙኒኮት ተጭዋቹን ለማዛወር በክረምት እንደሚንቀሳቀሱ እስካሁን ማረጋገጫ ሊሰጡት አለመቻላቸውን ተከትሎ በኢትሃዱ ክለብ የመቆየት እድል እንዳለው ምልክት መስጠት ጀምሯል። (mcgrathmike)
────────────────────────
▷ ስሙ ከአርሰናል ዝውውር ጋር የተነሳው የብሬንትፎርድ አጥቂ ኦሌ ዋትኪንስ: “አንድ ቀን ለአርሰናል መጫወት ህልሜ ነው። ሆኖም ይሄን እውን ለማድረግ ብዙ መንገድ እንደሚቀረኝ ታቁታላችሁ” (London Football Awards)
────────────────────────
▷ የፈረንሳይ እግር ኳስ ማህበር ከክለቡ ፒኤስዤ ኮከባቸው የ21 አመቱ አጥቂ ኬይላን ምባፔ በቀጣይ ክረምት በጃፓን በሚደረገው የኦሎምፒክ ውድድር ላይ ፈረንሳይን ወክሎ እንዲሳተፍ እንደማይፈልጉ በደብዳቤ አሳውቀዋል። (ESPN)
────────────────────────
▷ ኬቨን ዲ ብርየን እንደሚያምነው ከሆነ በቀጣይ እሁድ በሚደረገው የኦልትራፎርዱ የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ያለውን ተስፋ ገልፃአል።
(Daily Mirror)
────────────────────────
▷ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በክረምት ላይ ወደ ኤሺያ በማቅናት ለአዲሱ የውድድር አመት ዝግጅት የሚያደርጉትን የቅድመ ውድድር ጉዞ በኮረና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ለመሰረዝ ይገደዳሉ። (Sun)
────────────────────────
▷ የፕሪሚየር ሊጉ በተጭዋቾች እና ዳኞች መሃል የሚደረገው የወዳጅነት የእጅ ለእጅ መጨባበጥ ስረአት ከዚህ ስምንት የሊጉ ጨዋታዎች በኃላ በኮረና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ጭብብጡ እንደማይደረግ ታውቋል።
(premierleague)