
26/06/2025
ኤማን የበገና ማሰልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ከኒውማ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር የበገና ትምህርት እና የበገና ሕክምና (ቴራፒ) ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
የመግባቢያ ስምምነቱን የኤማን በገና ማሰልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ባለቤት እና ሥራአስኪያጅ መ/ር ኤርሚያስ ኃይላይ እና የኒውማ ኢትዮጵያ በጎ አድርጎት ድርጅት መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዘክርስቶስ ጸጋዬ ተፈራርመዋል።
የስምምነቱ ዓላማ ለኒውማ ኢትዮጵያ በጎ አድርጎት ድርጅት ሰራተኞች እና ሕሙማን የበገና ትምህረት እና የበገና ሕክምና (ቴራፒ) አገልግሎት ለመስጠት እና የጋራ ግንኙነትንና መግባባትን ማዳበርና አብሮ ለመስራት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
#በገና #ኤርምያስበገና
ethiopia.rehab_center