05/06/2026
"ለሁሉም ክፍት ከ17 አመት በላይ የክ/ከተሞች ቦክስ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ይካሄዳል"
በአዲስ አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በመዲናችን አዲስ አበባ ለሁሉም ክፍት የሆነ በ ኤ እና ቢ ተከፍሎ በሁለቱም ፆታዎች የክፍለ ከተሞች እና የቡድኖች ውድድር በአራዳ ፓርክ ፒያሳ አሬና ስፖርት ማዕከል ይካሄዳል::
ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 6/2018ዓ.ም በሚካሄደው ውድድር በርካታ ቦክሰኞች ይሳተፋሉ::
በዚህ ለሁሉም ክፍት የክ/ከተሞች ውድድር በሁለት ጎራ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን በ ኤ በቢ እንዲሁም በሴቶች ውድድሩ ይካሄዳል::
ውድድሩ በእያንዳንዱ ካታጎሪ ከአንድ ቡድን በየካታጎሪያቸው በኤ አንድ እንዲሁም በቢ አንድ ቡጢኛ ብቻ የሚያሳትፉ ይሆናል::
በዚህ ውድድር የምትሳተፉ በየክፍለከተሞቹ ያላቹ አሰልጣኞች የተወዳዳሪዮቻቹን ስም ዝርዝር እስከ ፊታችን እሁድ ግንቦት 30/2018ድረስ በዚህ+251918096107 የቴሌግራም ቁጥር ማስገባት ትችላላቹ::
"Open Boxing Tournament for All"
Organized by the Addis Ababa Boxing Federation, an open boxing tournament for all projects, sub-cities, and teams will be held in our capital city, Addis Ababa, at Arada Park – Piassa Arena Sports Center.
The competition will take place from Sene 2 to Sene 6, 2018 E.C. (Ethiopian Calendar) and is expected to be an exciting and vibrant event. 🥊🏆