Zebra Communications

Zebra Communications Zebra Communications works for the better enhancement of the community via communication platforms.

የመዝናኛ ሚዲያው ስኬታማ ፋና ወጊ አርፏል😭😭የኢቢኤስ ቴሌቪዥን አባት። የጀርባው ምሰሶ። ቅን፣ ተባባሪ፣ ዘመናዊ ሰው። ተቋም ሰርቶ አለፈ። አማን ለቴሌቪዥን ተመልካቾች የቤተሰብ ጉዳይ፣ ማኅበ...
11/02/2026

የመዝናኛ ሚዲያው ስኬታማ ፋና ወጊ አርፏል😭😭

የኢቢኤስ ቴሌቪዥን አባት። የጀርባው ምሰሶ። ቅን፣ ተባባሪ፣ ዘመናዊ ሰው። ተቋም ሰርቶ አለፈ። አማን ለቴሌቪዥን ተመልካቾች የቤተሰብ ጉዳይ፣ ማኅበራዊ ጉዳይ፣ መተዛዘን-መደጋገፍ በፈጠራ እየተከሸነ ትውልድ እንዲሰራበት የራሱን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቶ አለፈ።

ኢቢኤስ ቴሌቪዥንን በመመስረት፣ በመምራት የቤተሰብ እና የመዝናኛ ቴሌቪዥን ሰጥቶን አለፈ። የማይታወቅ ግን የማይዘነጋ ሰው ነዉ- አማን። ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን። ለወዳጅ ዘመዶችህ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን።

የዛሬ 22 ዓመት የተወለደው ፌስቡክ ከሃርቫርድ መኝታ ክፍል እስከ ሜታቨርስልክ የዛሬ 22 ዓመት፣ ዓለማችንን ለዘላለም የቀየረው "TheFacebook" በማርክ ዙከርበርግ እና ጓደኞቹ እጅ በሃ...
04/02/2026

የዛሬ 22 ዓመት የተወለደው ፌስቡክ ከሃርቫርድ መኝታ ክፍል እስከ ሜታቨርስ

ልክ የዛሬ 22 ዓመት፣ ዓለማችንን ለዘላለም የቀየረው "TheFacebook" በማርክ ዙከርበርግ እና ጓደኞቹ እጅ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነው የመወለዱ ታሪክ የሚጀምረው።

ዛሬ ግማሽ የዓለም ሕዝብ ወይም ከ3.27 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የሚገናኙበት ግዙፍ ዲጂታል መንደር ሆኗል።

ይህ አስደናቂ ጉዞ በ2003 "Facemash" በሚል የፎቶ ንጽጽር ሙከራ ተጀምሮ፣ ዛሬ ዋትስአፕንና ኢንስታግራምን ወደሚያጠቃልለው "ሜታ" (Meta) አድጓል።

ፌስቡክ በ2005 "The" የሚለውን ቃል ለማስወገድ 200 ሺህ ዶላር ሲከፍል፣ በ2009 ደግሞ የዲጂታል ዘመን ስሜት መግለጫ የሆነውን "ላይክ" (Like) ቁልፍ አስተዋውቋል።

ከማኅበራዊ ትስስር አልፎ በ2021 ራሱን ወደ "ሜታቨርስ" በማሸጋገር የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ዓለም እየመራ ይገኛል።

ከቤተሰብ ናፍቆት መወጫነት እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ መድረክነት የዘለቀው ፌስቡክ፣ ዛሬ የሁላችንም የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ሆኗል።

እስኪ ትዝታችንን እናድስ፦ እርስዎ ፌስቡክን መጠቀም የጀመሩት በስንት ዓመተ ምሕረት ነበር? መጀመሪያ የለጠፉትን ነገር ወይም የመጀመሪያውን የፌስቡክ ጓደኛዎን ያስታውሳሉ?
ሀሳብዎን በኮሜንት ያጋሩን!

04/02/2026

"ክልሉን በሚመጥን መልኩ በ 6ቱም ማዕከላት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በትኩረት ይሰራል"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

"የክልሉ መንግስት የክልሉን ሕዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና አብሮ የመልማት ትልም ዕውን ለማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት በበርካታ ዉጤቶች የታጀበ ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በክልላችን በየማዕከላቱ ታቅደው ተገቢውን ሂደት በማለፍ በግንባታ ላይ የሚገኙት የተቋማት ህንፃ ግንባታዎች፤ በጠንካራ የተቋማት ግንባታ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለጀመርናቸዉ ስራዎች አበርክቷቸዉ የጎላ ነዉ።

ፕሮጀክቶቹ የክልሉን የአስፈጻሚ ተቋማት ተቋማዊ አቅም በማጠናከር፤ ለክልላዊ የልማትና የብልጽግና ራዕይ ስኬት የላቀ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ በጥራትና በፍጥነት ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድመዉ እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት የሚከታተላቸው ይሆናል።"

24/12/2025
16/08/2025

Address

Bole
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zebra Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category