
09/04/2025
ክርስትና በጥያቄ ተጀምሮ በመልስ የሚፈጸም ጉዞ ነው ። ፍትሐዊነትን በሰው ነፍስ ያስቀመጠ እግዚአብሔር ፍትሕን አዘገየ ብሎ ማዘን ተገቢ አይደለም ።
እግዚአብሔር የፍጥረቱን ሁሉ ገደብ የለሽ ጥያቄ ፈርቶ አያውቅም ። እሱ እግዚአብሔር ጥያቄአችንን ስለማይቀየም በፍቅር ይመልስልና ። ሊያውም ለጆሮአችን ሳይሆን ለልባችን ይናገራል ።
በጸሎት በጽናት ለሚሞግተው ሁሉ፣ እግዚአብሔር በርሕረሠሔ ስለሚመልስ በምስጋና አፉን ይሞላል። ችግሮች ተወግደው ሳይሆን ችግሮቹ እያሉ እግዚአብሔር ማስደሰት ይችላል። እግዚአብሔር ችግሩን ትቶ እኛን በመለወጥ ይሠራል ።
ከወጀቡ በፊት የሐዋርያትን የልብ ጥርጣሬ የገሠጸው ከውጭው ማዕበል የውስጡ ማዕበል ስለሚበረታ ነው ። ነገሮች እንዲለወጡ ብቻ ሳይሆን አንተ እንድትለወጥ ለምን።
ማቴ. 8፡26 ።