22/05/2026
በጉጂ ዞን ለህዝብ ጥቅም የተገነቡ 207 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጁ!
የኦሮሚያ ክልል መንግስት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እየሰራ መሆኑን የጉጂ ዞን አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ነጋሽ ቡላላ ገለፁ።
በዚህ መሠረት በጉጂ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች በዚህ ዓመት ሲገነቡ የነበሩ ለህዝብ ጥቅም የሚውሉ ፕሮጀክቶች ለምረቃ ዝግጁ ሆነዋል።
እንደ አቶ ነጋሽ ገለፃ፣ ፕሮጀክቶቹ በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለአገልግሎት እየቀረቡ ሲሆን ህብረተሰቡም ከተጀመረው የልማት ለውጥ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል ብለዋል።
በ2018 ዓ.ም ብቻ በመንግስት በጀትና በዜጎች አገልግሎት 450 ፕሮጀክቶችን በ4.1 ቢሊዮን ብር ለማከናወን ታቅዶ እስካሁን 207 ፕሮጀክቶች ከ2.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተጠናቀው ለምረቃ መዘጋጀታቸው ተገልጿል።
📌 እነዚህ ፕሮጀክቶች በቅርቡ በመጀመሪያ ዙር ተመርቀው ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናሉ ተብሏል።