ምስለ ጎንደር

ምስለ ጎንደር የጎንደር በፎቶ ድንቅ ምስሎች

የሐምሌ 13 ትዉስታዎች •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••ዛሬ ሐምሌ 13 ነዉ ሐምሌ 13 ደግሞ በፋሲል ከነማ እግርኳስ ታሪክ ምናልባትም ከምስረታው ቀን ...
20/07/2024

የሐምሌ 13 ትዉስታዎች
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዛሬ ሐምሌ 13 ነዉ ሐምሌ 13 ደግሞ በፋሲል ከነማ እግርኳስ ታሪክ ምናልባትም ከምስረታው ቀን ጋር የምትስተካከል አንፀባራቂ ቀን ናት፡፡ አፄዎቹ ከተመሰረተበት 1960 ጀምሮ ብዙ አስደሳች ጊዜዎችን፣ በርካታ መሰናክሎችን፣ የተለያዩ ዉጣዉረዶችን፣ እና የተለያዩ ስያሜዎችን እያስተናገዱ በልጆቹ ፅናት አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ክለባችን ላለፉት በርካታ አመታት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ደረጃ የሚሰጠውን ፕሪምየር ሊግ ለመቀላቀል ጫፍ ላይ ደርሶ ሳይሳካለት በሩን እያንኳኩ ሲመለሱ ከርመዋል፡፡ ሆኖም ግን የዛ ሁሉ ድካም እና ጥረት ፍሬ ያፈራዉ ልክ የዛሬ ስምንት አመት በዛሬው ቀን ሐምሌ 13 2008 ዓ/ም ነበር። ይህ ወቅት ከተማችን ጎንደር በከፍተኛ የጭንቅ ምጥ ዉስጥ የነበረችበት ወቅት ሲሆን እንኳን ለሰላማዊ እግር ኳስ ጨዋታ ቀርቶ ወጥቶ ለመግባት እንኳ አስጊ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ዉድድሩን የሚያካሂደው አካል ጨዋታው እንዳይደረግ ቢወስኑም የከተማችን ከንቲባን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ሐላፊነት በመዉሰድ ጨዋታው በተያዘለት ቀን እንዲደርግ ተወሰኖ ቀኑ ተቆረጠ፡፡ እናላቹ ልክ የዛሬ ስምንት አመት አፄዎቹ ኢትዮጵያ መድህንን ሊገጥም አንድ ሁለት ሰአት ሲቀር ከፍተኛ ዝናብ መዝነብ ጀመረ፡፡ በዝናቡ ወቅታ በቋራ በኩል ሁነዉ ሲጨፍሩ የነበሩ ደጋፊዎችና በዛ ቅዝቃዜ ወቅት ከደጋፊዎቹ ሲወጣ የነበረዉ ጭስ እና ወኔ መቸም ሊጠፋ የማይችልና በህሊና ተቀርፆ ለረጅም ዘመናት የሚቆይ ትዉስታ ነዉ፡፡ በዝናቡ ምክንያት በዉሐ የተሞላውን ሜዳ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶች ከሜዳዉ ላይ የነበረዉን ከፍተኛ መጠን ያለዉ ዉሐ በባልዲ፣ በጆክ፣ በጆንያ፣ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች የውሃዉን መጠን ቀንሰዉ የጨዋታው ዳኞች የሜዳውን ሁኔታ ገምግመዉ ሜዳዉ ለጨዋታ ብቁ እንደሆነ ወስነዉ የጨዋታዉን መጀመር በፊሽካቸዉ አበሰሩ፡፡ አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ለደጋፊ መቀመጫ አይደለም መተንፈሻ ቦታ እስኪታጣ እንኳ በሞላበት ጨዋታ በአፄዎቹ በኩል በርካታ የጎል ማግባት አጋጣሚዎችን ሲያባክኑ ቆይተዉ የጨዋታው መገባደጃ ሰአት ላይ አመለ ሸጋዉ የመሐል ተጫዋቻችን ይስሐቅ መኩሪያ ከማዕዘን የተሻገረችዉን ኳስ በማስቆጠር ወደ ሊጉ ማደጋችንን ያረጋገጠች ጎል አስቆጠረ፡፡ በዛን ወቅት ጎሉ ሲቆጠር በስታዲየሙ የነበረዉ ታዳሚ ያሰማዉ ጩኸት ማንኛዉንም ተግዳሮቶች የመናድ አቅም አለዉ፡፡ የጨዋታው መጠናቀቅ ከተበሰረበት ደቂቃ በኃላ የነበረዉ ትእይንት ደግሞ ሌላ ትዉስታ ዉስጥ ይከታል፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሜዳው ጭቃ ላይ ሲንሸራተቱ ማየት ፋሲል ከነማ ምን ያህል ከክለብ በላይ እንደሆነ አመላካች ነዉ፡፡ እናም እኛ አፄያዊያን የዛሬን ቀን በዚህ መልክ እናስታዉሳታለን🇦🇹፡፡

እንኳን አደረሳችሁ ፋሲላዊያን🇦🇹❤️

ወርሀ ጥር ጥምቀትን በጎንደር📷 Meke z fasil
01/01/2024

ወርሀ ጥር ጥምቀትን በጎንደር
📷 Meke z fasil

የምስለ ጎንደር ሀይኪን አጋር ስፖንሰርDj root Entertainment 🇪🇹ሠርጋችሁን አንዲሁም ልዩ ልዩ ፕሮግራማችሁ ዲጄ ሩት ኢንተርቴመንት ምርጫዎ ያድርጉ 🎧For best and Qualit...
16/06/2023

የምስለ ጎንደር ሀይኪን አጋር ስፖንሰር
Dj root Entertainment
🇪🇹ሠርጋችሁን አንዲሁም ልዩ ልዩ ፕሮግራማችሁ ዲጄ ሩት ኢንተርቴመንት ምርጫዎ ያድርጉ 🎧
For best and Quality service

Mob 0911512898
RooRoot MeleselRoot Meleseራችን ስለሆንክ እናመሰግናለን 🙏

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምስለ ጎንደር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share