አንጎለላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ❴ Angolela tera Worda Prosperity party office❵

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • አንጎለላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ❴ Angolela tera Worda Prosperity party office❵

አንጎለላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት  ❴ Angolela tera Worda Prosperity party office❵ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አንጎለላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ❴ Angolela tera Worda Prosperity party office❵, Event Planner, Ethiopia, Debre Birhan.

"የህግ ማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የሰሜን ሸዋ ዞን ጠቅላላ አመራር የባለፋት ወራት የሰላምና ልማት ስራዎችን ገምግሟል ። በግምገማውም በቀጠናው ...
27/10/2025

"የህግ ማስከበር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን"

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር

የሰሜን ሸዋ ዞን ጠቅላላ አመራር የባለፋት ወራት የሰላምና ልማት ስራዎችን ገምግሟል ።

በግምገማውም በቀጠናው እየተከናወነ ያለውን ዝርዝር የህግ ማስከበር እና የልማት ስራ አፈፃፀም ቀርበው ተገምግመዋል ።

በየወረዳው እና ከተማ አስተዳደሮች የተከናወኑ የሰላምና ልማት ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እንዳሳዩም ተመላክቷል።

ቀበሌን ማዕከል ያደረገ ህዝባዊ ውይይቶች ፣ ወረዳና ቀበሌ ራስን ማስቻል ፣ ህዝቡን የሰላሙ ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ላይ የተሰራው ስራ አበረታች ውጤት እንደተገኘባቸው ተገልጿል ።

በቀጣይም ይኸው ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ።
ከልማት ስራ ጋር በተያያዘ የመስኖ ፣ ተፈጥሮ ሃብት ቅድመ ዝግጅት ፣ ትምህርት፣ ጤና ፣ ገቢ አሰባሰብና ስራ እድል ፈጠራ ተግባራት በጥልቀት ተገምግሟል ።

በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ ራሱ ለለውጥ ተነሳስቶ መላ ህዝቡን በማነሳሳት የታቀዱ ግቦች ሁሉ እንዲሳኩ ርብርብ እንደሚደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል።

‎የአንጎለላ ጠራ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች "የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን"  በሚል መሪ ቃል ውይይት ሲደረግ ውሎ በቂ ተግባቦት ከተፈጠ...
27/10/2025

‎የአንጎለላ ጠራ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች "የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ቃል ውይይት ሲደረግ ውሎ በቂ ተግባቦት ከተፈጠረ በኋላ ተጠናቀቀ!!
ጥቅምት 17/2018ዓ,ም

27/10/2025
27/10/2025
27/10/2025
‎የአንጎለላ ጠራ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች "የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን"  በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።‎‎በዛ...
27/10/2025

‎የአንጎለላ ጠራ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች "የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባንዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

‎በዛሬው እለት የአንጎለላ ጠራ ወረዳ መንግስት ሰራተኞች "የውጭ ባዳዎችንና የውስጥ ባዳዎችን ቅዠት በማምከን አንፀባራቂ ድሎችን እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

‎የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ለሁሉም ነገር መጀመሪያና መጨረሻው ሰላም በመሆኑ ለሰላም የምንሰጠው ትርጉም የተለየ መሆን አለበት።

‎በየትኛውም መሰረታዊ መስፈርት አሸናፊው የሚያደርገን በንግግር ናበውይይት በመሆኑ ሁሉም የክልላችን ባለድርሻ አካላት የራሱን ድርሻ በመወጣት የክልላችንን ሰላም በጋራ በዘላቂነት ማረጋገት ይገባናል ብለዋል።

‎የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት አቶ ጎሳዬ ማሞ የመወያያ ሰነድ እያቀረቡ ሲሆን ሰነዱ አጠቃላይ ክልላዊ ፣አገራዊና ቀጣናዊ የሆኑ የሁኔታ ትንተና እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በመጠቆም በዝርዝር ለተሳታፊው በዝርዝር እያቀረቡ ነው ።

26/10/2025

የሹመት መረጃ ፤

የአብክመ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ከጥቅምት 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የክልል ተቋማት አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል ።

ሹመት የተሰጣቸው አመራሮች የአመራር ብቃት፣ የስራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እና ስነ ምግባራቸውን መሰረት በማድረግ ነው።

በዚህም መሰረት :-

1. ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ ፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ

2. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ፡ የግብርና ቢሮ ኃላፊ

3. አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ፡ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አታላይ ጥላሁን፡ የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ

5. ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ መኮነን፡ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ

6. ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶ/ር ሞላ መልካሙ፡ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ

8. ዶ/ር መንገሻ ፈንታው፡ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ አባይ መንግስቴ፡ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አሰፋ ሲሳይ ተሾመ፡ የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

11. ዶ/ር ማተቤ ታፈረ፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት

12. አቶ እሱባለው መሰለ ፀጋየ፡ የአማራ ስቴት ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዚዳንት

13. አቶ እርዚቅ ኢሳ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ህዝብ ግንኙነት አማካሪ

14. አቶ ይትባረክ አወቀ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ

15. ዶ/ር ዘላለም ልጃለም፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደሩ ፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ

16. ዶ/ር ፈንታየ ጥበቡ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ

17. ዶ/ር ወልደትንሳኤ መኮነን ፈለቀ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አማካሪ

18. ዶ/ር ሰይድ እሸቴ፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የመሬት ቢሮ አማካሪ

19. አቶ አብይ አበባው ተስፋሁን፡ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳድሩ ስትራቴጂክ ዘርፍ አማካሪ

20. ዶ/ር ምትኩ አለማየሁ፡ የፕላን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር

21. አቶ ወርቁ ያየህ፡ የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

22. አቶ አዲስ በየነ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ኃላፊ

23. አቶ አየልኝ መሳፍንት፡ የግብርና ቢሮ መስኖ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

24. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው፡ የግብርና ቢሮ ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

25. ወ/ሮ እታገኝ አደመ ገላው፡ የግብርና ቢሮ ምግብ ዋስትና ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

26. አቶ ዘውዱ ማለደ፡ የመንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

27. አቶ ጋሻው ተቀባ፡ የባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

28. አቶ ዘላለም አረጋ ፡ የሴ/ህ/ወጣቶች ቢሮ ወጣት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

29. አቶ ነጋ ይስማው፡ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

30. ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን ፡ የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

31. ወ/ሮ ስመኝ ዋሴ፡ የስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

32. አቶ ጋሻው እሸቱ፡ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደሩ ህዝብ ግንኙነት ረዳት አማካሪ

33. ዶ/ር ተስፋሁን ተናኘ ፈሩህ፡ የፕላን ኢንስቲቲዩት ምክትል ዳይሬክተር

34. አቶ ገ/ማርያም ይርጋ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ

35. ወ/ሮ የሺ ካሴ፡ የባህል፣ ኪነ ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በመሆን ሹመት ተሰጥተዋል ።
•••
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•••

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•••
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

ከቡልጋ ክላስተር ወረዳዎች የተወጣጡ የሰላም አሰከባሪና ፖሊስ ሰልጣኞች የምረቃ ፕሮግራም ተካሄደ።      ጥቅምት 16/2018ዓ,ምበሰ/ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ  የስልጠና ማዕከል ሲሰጥ የቆየው...
26/10/2025

ከቡልጋ ክላስተር ወረዳዎች የተወጣጡ የሰላም አሰከባሪና ፖሊስ ሰልጣኞች የምረቃ ፕሮግራም ተካሄደ።
ጥቅምት 16/2018ዓ,ም

በሰ/ሸዋ ዞን አንጎለላ ጠራ የስልጠና ማዕከል ሲሰጥ የቆየው የተወርዋሪ ሰላም አስከባሪና ፖሊስ አባላት ስልጠና ተጠናቆ ዛሬ በተለያዩ ፕሮግራሞች የምረቃ ፕሮግራም ተካሂዷል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የሰ/ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ፣የሰ/ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ፣የመከላከያ ሰራዊት አመራር ኮረኔል አደራጀው ሰረበ፣ኮ/ል አየልኝ አስናቀ፣የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሃላፊ አቶ ይደሰቱ ክፈተው፣የሰ/ሸዋ ዞን ሚሊሻ ፅ/ቤት አቶ ሰለሞን አልታዩ ፣የሰ/ሸዋ ዞን ሴቶች ህፃናት መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ የሮምነሽ ጋሻው ጠና ፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረሰ ደመመን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካና የፀጥታ አመራሮች ተገኝተው ለሰልጣኞችን አስመርቀዋል።

የቡልጋ ክላስተር ራስን የመቻል የሰላም አስከባሪና የፖሊስ አባላት የማጠናከሪያ ስልጠና በድምቀት የተካሄደ ሲሆን በስልጠናው ላይ የተሻሉ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እና ልሎችንም ጨምሮ የምስጋና እና እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በመጨረሻም የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ የስራ መመሪያና ማጠቃለያ በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው::በአንጎለላና ጠራ ወረዳ የፋይዳ ምዝገባ ስራው በተለያዩ ቀበሌዎች ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።በአንጎለላና ጠራ ወረዳ "ጨኪና ፊጦ...
26/10/2025

የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው::

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ የፋይዳ ምዝገባ ስራው በተለያዩ ቀበሌዎች ዛሬም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ "ጨኪና ፊጦ" ቀበሌዎች በዛሬው እለት የፋይዳ መታወቂያ ማስመዝገብ ስራው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

Address

Ethiopia
Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንጎለላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ❴ Angolela tera Worda Prosperity party office❵ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category