Atnaf Promotion and Events

Atnaf Promotion and Events Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Atnaf Promotion and Events, Event Planner, Southwest, Bonga.

‎በጎንደር የሰላም ጥሪ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው‎‎*********************************‎(ሕዳር 25/2018 ቦንጋ አጥናፍ ፕሮሞሽንና ኢቨንት) የጎንደር ከተማ እና የማዕ...
04/12/2025

‎በጎንደር የሰላም ጥሪ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

‎*********************************
‎(ሕዳር 25/2018 ቦንጋ አጥናፍ ፕሮሞሽንና ኢቨንት) የጎንደር ከተማ እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በጋራ ያዘጋጁት የሰላም ጥሪ የድጋፍ ሰልፍ በዛሬው ዕለት እየተካሄደ ነው።

‎በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ባለው የሰላም ጥሪ ሰልፍ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

‎በሰልፉ ላይ ሰላምን ለማጽናትና አብሮነትን ለማጠናከር የሚያስችሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

‎በዚህም የሃይማኖት ተቋማት የሚያደርጉት ውይይት ግጭትን ለመፍታት ወሳኝ መሳሪያ ነው! ቤተእምነቶች ሰላም ማስፈን ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው! ሰላም፣ አንድነትና አብሮነት ከሃይማኖት ተቋም የተቀዱ ናቸው! የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።

‎በተጨማሪም ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን የአብሮነታችንና የጥንካሬዎቻችን መሰረቶች ናቸው! ሃይማኖት የሰላም መሰረት ነው! የሰላምና የመከባበር ባህልን ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ሚና የማይተካ ነው! በሚል መልዕክት በማስተላለፍ ህብረተሰቡ ለሰላምና አብሮነት ያለውን ፍላጎት አንጸባርቋል።
‎ዘገባው የአሚኮ ነው

‎20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በ' ወንድማማችነት ቀን' መከበር ጀመረ ‎‎ሕዳር 25፣ 2018 ቦንጋ አጥናፍ ፕሮሞሽንና ኢቨንት) 20ኛው‎‎በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ...
04/12/2025

‎20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በ' ወንድማማችነት ቀን' መከበር ጀመረ

‎ሕዳር 25፣ 2018 ቦንጋ አጥናፍ ፕሮሞሽንና ኢቨንት) 20ኛው

‎በዓሉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ
‎ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

‎በዛሬው ዕለት የሚከበረው የወንድማማችነት ቀን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በሩጫ ውድድር ተጀምሯል።

‎በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች እና አትሌቶች የሚሳተፉበት የ5 እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩን ኮማንደር አትሌት ሰለሞን ባረጋ አስጀምሮታል።

‎በአትሌቶች ምድብ የ10 ኪሎሜትር ውድድር የሚካሄድ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎች በ5 ኪሎሜትር እየተሳተፉ ነው።

‎ዘገባው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ነው

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማርኮ ሩቢዮ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።***********...
04/12/2025

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ።
*****************************
አጥናፍ ፕሮሞሽንና ኢቨንት (ህዳር 25/2018 ዓ/ም ቦንጋ)

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዋና ምክትል ቃል አቀባይ ቶሚ ፒጎት ማምሻውን እንደገለጹት፣ የሁለቱ ባለስልጣናት ውይይት ትኩረቱን ያደረገው በቀጠናዊ መረጋጋት እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንደገለጸው፣ በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በተለይም ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች በሚታዩበት የአፍሪካ ቀንድ፣ የሰላም መሰረትን ለመጣል እና ትብብርን ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

ይህ የስልክ ውይይት እና ከሰሞኑ ኢትዮጵያን ከጎበኙት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ እዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን ጋር ተያያዞ፣ በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራርቦ ለመስራት ያለመ መሆኑን ከተለቀቀው መግለጫ መረዳት ይቻላል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

በምንከተለው የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፎች ቀጣይነት ያለው በእጅጉ እያደገ  የሚሄድ በማህበረሰብ ለውጥና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ዕድገት  በማስመዘገብ  ሁለንተናዊ ብልፅግና  ልና...
27/11/2025

በምንከተለው የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ በሁሉም ዘርፎች ቀጣይነት ያለው በእጅጉ እያደገ የሚሄድ በማህበረሰብ ለውጥና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ዕድገት በማስመዘገብ ሁለንተናዊ ብልፅግና ልናረጋግጥ ይገባል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ስሰጥ የነበረው 2ኛ ዙር ሀገር ዓቀፍ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቋል።

“በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መርህ ቃል ላለፋት ዘጠኝ ተከታታይ ቀናት በቦንጋ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና የአመራሩን እውቀት፣ ክህሎትና የመፈጸም አቅም በሚገነቡ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ያተኮረ እንደነበረ ተገልጿል።

በስልጠናው ማጠቃለያ ተገኝተው በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በማኅበረሰቡ ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ አመራሩ የአስተሳሰብና የባህር ለውጥ ማምጣት አለበት ብለዋል።

በምንከተለው የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ሂደት በሁሉም ዘርፎች ቀጣይነት ያለው በእጅጉ እያደገ የሚሄድና በማህበረሰብ ለውጥና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተጨባጭ ዕድገት በማስመዘገብ ሁለንተናዊ ብልፅግና ልናረጋግጥ ይገባል ስሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

አመራሩ በትናንሽ ድሎች ሳይዘናጋ በትልቁ አቅዶ አልቆ መፈጸም አለበት ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ከራስ የሚጀምር የሥራ ባህል ማሻሻል ይጠበቃል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኘው አመራር ከጠባቂነት በመላቀቅ፣ ማኅበረሰብን በማስተባበር እንዲሁም በራስ አቅም ፈጠራና ፍጥነት በማከል በውጤት የታጀበ ተግባር መፈጸም እንደሚጠበቅበትም ነው ያስገነዘቡት።

ህዝብን ለማገልገል በተሰጠው አጭር ጊዜ አሻራ ጥሎ ማለፍ ከእያንዳንዱ አመራር እንደሚጠበቅ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ውጤት አልቦ በኾኑ ተግባራት ጊዜ ማጥፋት እንደማይገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።

መልካም ተሞክሮዎችን ማስፋትና በሁሉም ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የተጀማመሩ የኢንሼቲቭ ተግባራትን ቀጣይነት ባለው መልኩ አጠናክረው ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የግብርና ሽግግር በማሳለጥ የገጠር ሽግግርን በተጨባጭ ማረጋገጥ እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ግብርናን በማዘመን ለጠቅላላው ሃገራዊ ምርት የሚያበረክተውን ድርሻ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

አመራሩ ተግባራት የመፈጸም አቅም በማጎልበት ከወቅቱ ጋር አብሮ መጓዝ እንዳለበት በማመልከት እያንዳንዱን ተግባራት በፈጠራ፣ ፈጥነትና በዝላይ መፈጸም እንዳለበትም ተናግረዋል።

በመደመር መንግሥት መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣትና የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ እንዲሳካ የአመራር ሚና ወሳኝ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ አመራሩ ለወቅታዊ ችግሮች ሳይበገር የመፍትሔው ምንጭ መኾን አለበት ብለዋል።

አመራሩ በወሰደው ስልጠና የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በማከል በቀጣይ የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረትና ትጋት መስራት እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል

ዘገበው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በነጌው እለት በቦንጋ ከተማ  ደረጃ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች  በታላቅ ድምቀት ይከበራል።የቦታ ዝግጅቱም ተጠናቋል።
18/11/2025

20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በነጌው እለት በቦንጋ ከተማ ደረጃ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

የቦታ ዝግጅቱም ተጠናቋል።

‎ #ሳፋሪኮም ቦንጋ ስራ መጀመሩን ያውቁ ኖሯል?‎******************************‎ #ሁለተኛው የቴለኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በተለያዩ ትላልቅ ከተሞች አገልግሎት እየሰጠ ቆይቶ በ...
29/10/2025

‎ #ሳፋሪኮም ቦንጋ ስራ መጀመሩን ያውቁ ኖሯል?
‎******************************
‎ #ሁለተኛው የቴለኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በተለያዩ ትላልቅ ከተሞች አገልግሎት እየሰጠ ቆይቶ በቦንጋ ከተማና አካባቢው የኔትዎርክ ዝርጋታ አጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል።

‎ሁላችንም የሳፋሪኮም ተጠቃሚ እንሆን።

Address

Southwest
Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Atnaf Promotion and Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category