
18/08/2020
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ 10 ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድበዛሬው ዕለት 10 ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚሁ መሰረት፦
1. ዶ/ር ቀንዓ ያደታ- የመከላከያ ሚኒስትር
2. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ- ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
3. ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
4. ኢንጂነር ታከለ ኡማ- የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር
5. አቶ ተስፋዬ ዳባ- ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ
6. አቶ ዮሐንስ ቧያለው - የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት
ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
7. አቶ ንጉሡ ጥላሁን - የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር
8. ኢንጅነር እንዳአወቅ አብቴ - የብረታ ብረትና ኢንጅኔሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና
ዳይሬክተር
9. አቶ ፍቃዱ ጸጋ - ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
10. ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማርያም - በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።