Saro Media Network

Saro Media Network ወቅታዊ ፣ ታማኝ እና ሚዛናዊ መረጃ የሚያገኙበት ገጽ ነው ‼️

የቁሕዴፓ የክልልን መዋቅር የመናቅ አደገኛ አካሄድ​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ስር የሚገኘው የቁጫ ምርጫ ክልል የራሱ የሆነ የጸጥታ መዋቅርና የክልል ፖሊስ ኃይል እያለው ቁሕዴፓ (የቁ...
17/04/2026

የቁሕዴፓ የክልልን መዋቅር የመናቅ አደገኛ አካሄድ

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ስር የሚገኘው የቁጫ ምርጫ ክልል የራሱ የሆነ የጸጥታ መዋቅርና የክልል ፖሊስ ኃይል እያለው ቁሕዴፓ (የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ) የፌዴራል ፖሊስን በቀጥታ አስገባለሁ ማለቱ ለክልሉ መንግሥትና ለሕዝብ ጸጥታ መዋቅር ያለውን ከፍተኛ ንቀት ያሳየበት ነው።

​በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሥርዓት መሠረት የአንድን አካባቢ ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ቀዳሚ ኃላፊነት የክልሉ መንግሥት ነው።

የክልሉ የጸጥታ መዋቅር ከአቅሜ በላይ ነው የሚል ጥያቄ ሳያቀርብና በሕግ አግባብ የፌዴራል ኃይል ሳይጠየቅ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ የፌዴራል ፖሊስን ማስገባት መፈለጉ ከክልሉ መንግሥት በላይ ነኝ የሚል ግብዝነት ነው። ይህ ድርጊት የክልሉን ፖሊስ ክብርና ብቃት ዝቅ አድርጎ የሚመለከት ነው።

​ቁሕዴፓ ለክልሉ አስተዳደርና ሕግ የማይገዛው ለምንድነው? መልሱ ግልጽ ነው በክልሉ ሕጋዊ አሠራር ውስጥ ሆኖ በሰላማዊ መንገድ መወዳደር ስላቃተው የፌዴራል ኃይልን እንደ ጋሻ በመጠቀም አካባቢውን ለመረበሽና የሁከት ቀጠና ለማድረግ እያሴረ ይገኛል።

የክልሉን ፖሊስ ገፍቶ የፌዴራል ፖሊስን መጥራት፣ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ያለውን መተማመን ለማፍረስ የታቀደ የፖለቲካ ደባ ነው።

​ፓርቲው የጸጥታ ስጋት የለም እያለ በሌላ በኩል የፌዴራል ፖሊስ ካልጠበቀኝ ማለቱ የንግግርና የተግባር ቅራኔውን ያሳያል። ይህ የሚያሳየው ፓርቲው የሕዝብ ድጋፍ እንደሌለውና በኃይል ታጅቦ የፍርሃት ድባብ ለመፍጠር መዘጋጀቱን ነው።

ሰላማዊ ምርጫ የሚካሄደው በሕዝብ አመኔታና በሕጋዊው የክልል የጸጥታ መዋቅር እንጂ በፓርቲ ፍላጎት በሚዘወር የኃይል ስምሪት አይደለም።

ቁሕዴፓ የክልሉን መንግሥት ሕጋዊ ሥልጣንና የጸጥታ መዋቅር በመናቅ የሚያደርገውን ይህን የጥፊ ፖለቲካ በጽኑ እንቃወማለን።

የክልሉ ፖሊስ የሕዝቡን ሰላም ለማስከበር ብቃትና ዝግጁነት እያለው ሆን ተብሎ የሚደረግ የፌዴራል ኃይል ጣልቃ ገብነት ፍፁም ተቀባይነት የሌለውና ለቀጣይ ቀውስ መነሻ የሚሆን ተግባር ነው።

ቁሕዴፓ ሆይ ለምርጫው የምትገዛው በክልሉ ሕግና መዋቅር እንጂ የራስህን መንግሥት በክልሉ ላይ ለመመሥረት በምታደርገው ሕገ-ወጥ ጉዞ አይደለም።

የክልሉን ፖሊስ መናቅ ሕዝቡን መናቅ ነው የሰላምበርን ሰላም ለማደፍረስ የምታደርገው የኃይል ፖለቲካ በሕዝብ ትግል ይከሽፋል

ሰበር ዜና :-የሆርሙዝ ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ክፍት ተደረገ::ሚያዚያ 9፣ 2018 :- አዲስ አበባ በመካከለኛው ምስራቅ ለወራት ዘልቆ የነበረውን ውጥረት ተከትሎ ተጥሎ የነበ...
17/04/2026

ሰበር ዜና :-የሆርሙዝ ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ክፍት ተደረገ::

ሚያዚያ 9፣ 2018 :- አዲስ አበባ በመካከለኛው ምስራቅ ለወራት ዘልቆ የነበረውን ውጥረት ተከትሎ ተጥሎ የነበረው የባህር ላይ ትራንስፖርት ገደብ መነሳቱን የኢራን መንግስት በይፋ አስታወቀ።

በእስራኤል እና በሊባኖስ መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደ መልካም አጋጣሚ የተጠቀመችው ኢራን፣ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ስታካሂድ የነበረውን የደህንነት ቁጥጥር በማላላት ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት ማድረጓን ገልጻለች።

ጋሞ ጨንቻ  አንድነት ፓርክን በመጎብኘት የመጀመሪያው ቡድን ሆነ!በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድብ ሀ 1ኛ በመሆን ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተቀላቀሉት ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ...
17/04/2026

ጋሞ ጨንቻ አንድነት ፓርክን በመጎብኘት የመጀመሪያው ቡድን ሆነ!

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከምድብ ሀ 1ኛ በመሆን ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተቀላቀሉት ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ አባላት በጅማ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው አዲስ አበባ ገብተዋል።

አፕሎቹ በዛሬው ዕለት አንድነት ፓርክንየጎበኙ ሲሆን ፓርኩን በመጎብኘት የመጀመሪያው የእግር ኳስ ቡድን መሆናቸውን አስጎብኚው ገልጸዋል።

የቡድኑ አባላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የተቀበሉት ወንድም ዘማች ጉማኣ የጉብኝት መርሃግብሩን በማመቻቸት አፕሎቹ የተዝናኖት ጊዜን እንዲያሳልፉ ማድረግ ችለዋል።

የቡድኑ አባላት በአድነት ፓርክ በተሰሩ አስደናቂ የልማት ስራዎች መደሰታቸውንም ተናግረዋል።

17/04/2026

እንዴት ደስ ይላሉ ❤

  🦁ኦ ጋሞ ታኒ ጋሞና ታኒ ጋሞና ዳንጋርሳ ባቤ ናጋዳርጋርሳ ታኒ ጦኒ አጋቴዲ አፍሮ 👏 #ፒንታጎ  #ኢቶሪካ
16/04/2026

🦁
ኦ ጋሞ ታኒ ጋሞና
ታኒ ጋሞና
ዳንጋርሳ ባቤ ናጋ
ዳርጋርሳ ታኒ ጦኒ አጋ
ቴዲ አፍሮ
👏
#ፒንታጎ
#ኢቶሪካ

የፀጥታ አካላትን ብቻ ለይተው በማውረድ ነው በጥይት ደብድበው የገደሏቸው ። ‎ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በአንድ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ፦አንድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ አባል ፣ አንድ የአዲ...
16/04/2026

የፀጥታ አካላትን ብቻ ለይተው በማውረድ ነው በጥይት ደብድበው የገደሏቸው ።

‎ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በአንድ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ፦

አንድ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፖሊስ አባል ፣ አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል፣አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባል ሲገደሉ ተሳፋሪዎች ላይ ዝሪፊያ መፈፀሙን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ማስታወቁን ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ታጁ ነጋሽ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው ሚያዚያ 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዓት ገደማ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በሱተንና ጥያ መሃል ' ቀሬ ' ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ነው።

ታጣቂዎች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪ በማስቆም ሶስት የመንግስት የፀጥታ አባላትን ገድለው ሌሎች ተሳፋሪዎችን መዝረፋቸውን ኮማንደር ታጁ ተናግረዋል።

‎በጥቃቱ ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ የተባሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከንባታ ዞን ከፍተኛ የፖሊስ መኮንን ጨምሮ አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል እና አንድ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል መገደላቸውን አስታውቀዋል።

‎ተሽከርካሪው መነሻውን ወላይታ ሶዶ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን የፖሊስ መኮንኗ ከመኖሪያቸው ዱራሜ ተሳፍረው ወደ አዲስ አበባ እየተጓዙ እንደነበር ታውቋል።

‎ታጣቂዎቹ ከላይ በተጠቀሰው ስፍራ ተሽከርካሪውን በማስቆምና የመንግስት የፀጥታ አካላትን ብቻ ለይተው በማውረድ በጥይት ደብድበው እንደገደሏቸው ተገልጿል።

ከሶስቱ የመንግስት የፀጥታ አባላት መካከል በኢትዮጽያ ሀገር መከላከያ ዩንቨርሲቲ ዋር ኮሌጅ በስትራቴጂክ አመራር ስልጠና ላይ የነበሩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ በሶስት ጥይት ተመተው መገደላቸውን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ አስረድተዋል።

የቀብር ስነ ስርዓታቸውም በፖሊሳዊ አሸኛኘት በዱራሜ ከተማ የተለያዩ ክልሎች የፖሊስ ኮሚሽነሮችና የፖሊስ አባላትና ወዳጅ ዘመድ በተገኙበት በወንጌላውያን አማኞች መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ኮማንደር አልማዝ ባለትዳር እንዲሁም የሁለት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ እናት ነበሩ።

‎የጥቃት አድራሾቹን ማንነት በሚመለከት " ፀረ ሰላም ሃይሎች " ከሚል በዘለለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ሆነ ሌሎች መዋቅሮች የገለፁት ነገር የለም። ሁሌም ቢሆን ጥንቃቄ አይለያችሁ !

ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶችና ለስራ ባልደረቦቻቸው በግዮን ማለዳ ስም መፅናናትን እንመኛለን ። ነብሳቸውን ይማርልን ።

Via፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 33

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 32

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 31

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 30

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 29

16/04/2026

100067323427557:2048:Saro Media Network Part 28

Address

Arba Minch'

Telephone

+251911238014

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Saro Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Saro Media Network:

Share