የኔታ ኪነ-ጥበባት እና ፕሮሞሽን

የኔታ ኪነ-ጥበባት እና ፕሮሞሽን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኔታ ኪነ-ጥበባት እና ፕሮሞሽን, Addis Ababa.

06/07/2023
https://youtu.be/h-LZatcevmM
04/11/2022

https://youtu.be/h-LZatcevmM

አንጋፋው ሙዚቀኛ ምንሊክ ወስናቸው (ጋሽ ጀምበሬ) በ1933 ዓ.ም አዲስ አበባ ተ/ሀይማኖት አካባቢ ተወለደ። በጓደኞቹ አማካኝነት ወደ ሙዚቃው አለም እንደገባ የሚናገረው ጋሽ ጀምበሬ። ስለ ስ.....

Subscribe z channel
28/02/2021

Subscribe z channel

የልቤን አዳራሽ #በሚለው ነጠላ ዜማ የምናውቀው #"ሳሙኤል ድንቁ" አዲስ ሙዚቃ # Samuel Dinku # new music

"ሐገር ያህላል÷ ከፍ ያለ ፍቅር"  እማ ዘንድ ይደር! ተምኔታዊ ዘፈን ነው፡፡ እውነታዊም፡፡ እንጉርጉሮው ሀያል ነው፡፡ የሐገርህ ሰው ሲያንጎራጉር መስማት አለብህ፡፡ የልቡን ይነግርኸል፡፡ እ...
15/05/2020

"ሐገር ያህላል÷ ከፍ ያለ ፍቅር"

እማ ዘንድ ይደር!

ተምኔታዊ ዘፈን ነው፡፡ እውነታዊም፡፡ እንጉርጉሮው ሀያል ነው፡፡ የሐገርህ ሰው ሲያንጎራጉር መስማት አለብህ፡፡ የልቡን ይነግርኸል፡፡

እኔ ይህን ቅኔ ልነካው እፈራለው፡፡ እንዳላበላሸው ብዬ፡፡ ከሀገር መቅደስ ለመግባት÷ ከግዙፍ የስነ ጥበብ የሐገር ግንባታ÷ አምሮት/ ቁጭት/ ጋር ለመቆም አቅሙ አለኝ ብዬ ስለማላስብ፡፡

ፈርቻለው፤ ግን ደግሞ ላንቦጫርቀው፡፡ የልጅ እራት ይሁንብኝ፡፡ እማ ዘንድ ይደር ድርሳንን ከመንካታችን በፊት÷ ስለ ፍቅር የተሰኘውን የተደጎሰ መፅሀፈ ዘፈንን እንስማ፡፡ ኹለቱ ዘፈኖች እናት እና ልጅ ይመስሉኛል፡፡ ሳይለያዩ መነበብ፤ መደመጥ ያለባቸው፡፡ በምን ያህል ሕመም ላይ ሆኖ ብዑሩ እንደታዘዘለት አላውቅም፡፡ ምን ያህል ነብሱ ስለ ሐገሩ ቢያማት በመስቀል ላይ ስለ ሀገሩ፤ ስለ ሰውነቱ ብትቃትትበት ይሆን እላለው፡፡ እንባዬ ይመጣል፡፡ ለቅሶ ህመምን ያሽራል፡፡

ቴዎድሮስ ካሳሁን÷ በስነ ግጥም ከፍታ ብዕራም ነው፡፡ ቅኔ ይችላል፡፡ ስለ ፍቅር እና እማ ዘንድ ይደር የተሰኙት ዘፈኖቹ በእንጉረጉሮ የሚከወኑ ናቸው፡፡ ጥያቄም፤ መልስም ይዘዋል፡፡ መልሱን አውቆት ነው የሚጠይቀው፡፡ መነሻውን፤ መዳረሻውን ያውቃል፡፡ ሁለቱ ዘፈኖች፤ የሊቅ ቅኔ ናቸው፡፡ አንድ ላይ ከተነበቡ÷ የከዋኙን የልቡና ፈቃድ ማግኘት ይቻላል፡፡

አምሳለ ጦቢያ፡-

የልቡን ፍቃድ ሐገር ይሰራል፡፡ መልክዐ ምድር አበጅቶ÷ የሐገሩን ሰንደቅ መርጦ÷ ከሰውም ሴት መርጦ÷ ከልብስሽም ሸማ ሰርቶ÷ በታሪክ አባይነት ውስጥ ይፈሳል፡፡ ከዘመንም÷ አክሱማዊነትን አንግቦ÷ ከትናንት ከዘረ አዳም እስከ ነገ ድረስ ይፈክራል፡፡ በ 11 ደቂቃ፤ በ 19 ሰከንድ ውስጥ፡፡

ሐገሩ የቆመበትን ሚት ይናገርበታል፡፡ ሴት ናት÷ ማክዳ የተሰኘች፡፡ በቁንጅናዋ የምታይ፤ የምትታይ ናት፡፡ መገለጥ የነበራት፡፡ የፍጥረት ማህፀን ሴት የሆነች፡፡ የምትወልዳቸው ልጆች ይሰራላታል ቆይቶ፡፡ ኢትዮጵያም ውክልናዋ በሴት ነው፡፡ ቴዲም ቀድሞ ከሰፈረው ሳባዊ ሀሳብ ተውሶ ያንጉራጉራል፡፡ ሳባዊ ነው ሀሳቡ፡፡ (ethio centrist myth)

መልከ ማክዳ ሳባ መሳይ÷
የብራና ስዕል አይነ ጎላየ፡፡

የማክዳ ሐገር ልምላሜ የጉበኘው ነው፡፡ መሬቱ ፍሬ የሚያፈራ፤ ኤደናዊ ያደርገዋል፡፡ የስልጣኔ ምልክትነቱን፤ የብልፅግና ቢትወደድነቱን ይመሰክርለታል፡፡ (Romanticize with the nation) አፈር ይዞ ውስጡ አረንጋዴ ይላል፡፡ ላይኛው የመሬት ክፍል ብቻ ሳይሆን÷ ውስጡም በተፈጥሮ በረከት የታደለ መሆኑን ያስታወሰናል፡፡ ሐገሩም መለያ ሰንደቁን ይመርጣል፡፡ ከሌላው የሰው ዘር በሸማ ያጌጠ መልኩን ያሳያል፡፡ (Myth became visible, and represented)

ቀስተ ደመና ነው የለበስት ጥበብ÷
የያስኩት አርማ፡፡

የማክዳ ሐገር÷ ምስለ ኢትዮጵያ÷ በታሪክ ምንጣፍ ተጉዞ÷ ከምስራች ታሪኳ ይልቅ÷ መርዶዋ በዝታል፡፡ በብልፅግና÷ የተራመደችው መንገድ መልኩን ቀይሮ÷ ዘመነ ችግር ላይ ደርሳለች፡፡ ዛሬ ላይ÷ ሐገሩ የቆመበት ትርክትም በአፍጢሙ ተደፍቶ÷ በደመና እና በምድር መኸል የሚንሳፈፍ ቅጠል ሁነናል፡፡

እንዲህ የሚወዳት÷ በምናቡ ብቻ ሳይሆን የምትታየው ሐገሩ "ዲኮንስትራክ" በሆነ መንገድ÷ ርቀዋለች፡፡ ፊዚካሊ ሳይሆን÷ መንፈሳ፡፡ የሐገሩ ልሂቃን÷ መልከ ማክዳ የሆነችውን ሐገር÷ የቀለመው ሰንደቁን ዋጋውን አሳንሰው÷ ሚታዊ ሪፕረዘንቴሽኑን ብለርድ ስላደረጉበት ያዝናል፡፡ ኢትዮጵያ/ ክፍለ ኢትዮጵያን/ ስለነጠቁትም፤ የውስጥ ቆዳው እስኪያመው ድረስ ይቀኛል፡፡ ህመሙ፤ ያማል፡፡ (Deconstruction of the nations)

ድር አስተርታሪ ጥልፍ የጠለፈው÷
አስዋብኩሽ ብሎ ምን አስጎበረው፡፡

ዛሬ እንደ ገና በአዲስ ትርክት እና በውክልናዊ ቀለም የተሰራው ሐገር ከትናንት እስከ ዛሬ መራመዱን ለመዘንጋታቸው የእውቀት እና የሞራል ሙግት ያቀርባል፡፡ ዛሬ÷ የትናንት ልጅ÷ የነገ ተስፋ መሆኑን ይቀኝበታል፡፡ እውቀት÷ ጥበብ እና ሐገርነት በተዋህዶ ይፈክርበታል፡፡ (Neo Traditional)

ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ ባትሮንሱ ላይ
የነ ፋሲለ ደስ የነ ተዋናይ
የት ጋር እንደሆን ይታይ የኛ ጥበብ መሰረቱ
የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ

ሐገረ መንግስቱ አዲስ ቅኝት ውስጥ ገብቷል፡፡ በጦርነት÷ በሰዎች እንቅስቃሴ÷ በገበያ ተጋምዶ፤ ተሳስሮ የኖረውን ለያይተውታል፡፡ አዲስ ኩሸት/ ሚት/ ተፈጥራል፡፡

የመኖሩ ምክንያት ሐገሩ ስለሆነችም÷ መስቀል ላይ የተቸነከረ ያህል ሆኖ÷ ስለ ራቀው መሬት÷ ስለ ሰው ይብገነገናል፡፡ መቼስ መሬት ማለት ብዙ ነገሩ ነው ለኢትዮጵያዊው፡፡ የኖረበት÷ የተወለደበት÷ የሰረገበት÷ ያረሰበት÷ የሚቀበርበትም ነው፡፡ ሰውን ከመሬቱ ላይ ሁነህ ምን እንደሚመስል መረዳት ይቻላል፡፡ የሰውነት ንባቡ ከመሬቱ ጋር ነው፡፡ ለሰው መሬት ሰሌዳ ናት፡፡ የተፈጠረውን ኮስሚክ ለውጡን ያለቅስለታል፡፡ ባለ ቅኔው ቴዲም እንዲህ ይላል÷

/አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል/

ሸማ ተጊጦ÷
ቀለም ቢነከር÷
ልብስ አያምርበት÷
ያ ራቁት ሐገር፡፡

በእንባ የሚናገረው ባለ ቅኔው÷ ቴዲ አፍሮ፡፡ ከህመሙ ቁስል ጋር መቆየት አይሻም÷ አይነ ገላዬ ለሚላት መልከ ማክዳ ሐገሩ እስትንፋስ ሊሰጣት የመድሀኒት ቅመማውን ይጀምራል፡፡ የሚሻለውንም ይመርጣል፡፡ ከመስቀል ተቸንክሮ መቅረት አይሻም፡፡ የዘፈኑ ትልቁ ልቡም በዚህ ቦታ ላይ ይገለጣል፡፡ የህግ ሁሉ ፍፃሜ ፍቅር ነው ብለን አስበን ነበር፡፡ ከፍቅር የሚበልጥ ተምኔት ግን አለ ይለናል÷ እሱም ሐገር ነው ብሎ በጣም በልዕልና ያሰቀምጣል፡፡ እንደ ማዕዘን ድንጋይ የከበረ ሐሣብ ይሰራል፡፡ ትልቁ ፍቅር ሐገር ነው፡፡ በየቤታችሁ መግቢያ ላይ አስፍሩት፡፡ በየልባችሁም ፃፉት፡፡ (ፍቅር÷ ሲሞላለት ሐገር ሆንኩኝ ይላል፡፡)

ልቤህ አምሮ ሌላ ዝቅ አትበል ይቅር÷
ሐገር ያህላል ከፍ ያለ ፍቅር
+
ማ ፃም ይዞ ቆጥሮ ጠጠር
ባሳከለው ፍቅርን ሐገር

ከፍቅር በላይ በሰማየ፤ ሰማያት ሐገሩን የሰቀለው ጥበበኛም÷ የመልከ ማክዳን ሐገር በመንፈሳዊ ኃብታት የዘወትር ፀሎት ያሰማባታል፡፡ የሐገሩ፤ የመልከ ማክዳው ፍቅር ማለቂያ የለውም፡፡ ከፍቅር ከፍ ያለ÷ ከራሱ ከማንነቱም የገዘፈ መሆኑንም ያሳየናል፡፡ ካለ ሐገር እርሱ ምንም እንደሆነ ያሳርጋል፡፡ 'ቶ' ፊደል ደግሞ ሰውን መወከል የምትችል ናት፡፡

ልቤ አንቺን ትቶ ከማን ዘንድ ይደር፤
ልማልልሽ ወይ በ 'ቶ' መስቀሌ
ከራሴው ጋር ነው ብጣላሽ ጥሌ

ማክዳ ሐገሩንም፤ ወደ ሰው ሁሉ ምድርነት ይቀይራታል፡፡ ግዛቷን፤ አሸናፊነቷን ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲሆንላት ይለምናል፡፡ ከአንድ የምድር ጥግ ይልቅ÷ ወደ አለም አቀፋዊነትም ይለወጣል፡፡ በሐገራዊ፤ በኢትዮጵያዊ ኃብታት ተነቅሶ÷ ለሰው ሁሉ ይዘምታል፡፡ ሐገሩን የነጠቁትን ጭምር ሊባርክ ይጋዛል፡፡ (Trans Ethiopia)

ልክ እንደ አክሱም ራስ ቀርፀሀት ነብሴን÷ በፍቅር ጣፍ ለኩሳት ነብሴን
በል አትዛል ቀና ሁን ልቤ÷ የዕድሜን ከነዐን እንዳይ ቀርቤ
ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ÷ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ፡፡

ቴዎድሮስ ካሳሁን ምኞቱ ማክዳን÷ ሐገረ ኢትዮጵያን በአይኑ በብሌኑ÷ በፍቅራ ተማሽታ÷ ለሰው ልጆች ኹሉ የተመቸች እንድትሆን÷ ከልቡ ተምኔት እስከ እጅ መዳሰስ ድረስ ተጉዛል፡፡ እስትንፋስ ዘርታ÷ ለሰው ልጆች ምኩራብ እንድትሆን ስለት ተስላል፡፡ ልክ እንደ ወንጌላዊው ቶማስም ማየት ፈልጋል፡፡ የፍቅሩ ኃያልነት በማየት እንዲገለጥም ፈልጋል፡፡

ስለት አለብኝ ከርቤ እና እጣን÷
ለመተያየት እንዲያበቃን፡፡

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ፡-

የእማ ዘንድ ይደር እና የስለ ፍቅር የቅኔ ገንቦዎች÷ እንደ ሰማይ የከበደ መልዕክት ለዛሬይቱ ኢትዮጵያውያን አስፍረውልናል፡፡
ሰው ለመውደድ እንዳንደክም እና ፍቅር አዛውንት ሲሆን ሐገር እንደሚያህል ይፈክርልናል፡፡ ከፍቅር የላቀ ሐገር የተባለ ተምኔትን÷ አብረን እንስራ፡፡

~ Girma Fetaw

15/05/2020

«ፍርሀት» - ሀቲት፡ ተረፈ አብደላ ዕዝራ! (ነፍስ ኄር

እንባዬን የት ላርገው(በእውቀቱ ሥዩም)ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀናከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁናጣራው ባጡ ቀርቦኝበር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝበጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨ...
15/05/2020

እንባዬን የት ላርገው
(በእውቀቱ ሥዩም)
ቀና በል ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው
ወዴት ልሸሽገው?

     #ነቅቻለሁ♥ነቅቻለሁ ተርፌያለሁእራሴን ላድን ቆርጫለሁልኩ ላይ ብርሀኑ ላይአይኔ ላፈዝ ጨለማው ላይልፈልገው ከዋለበትፍፁም ፍቅር ከሞላበትእራሱ ላይ ጎዳናው ላይፍቅርን ላገኝ ፊት ለፊት ...
05/10/2019

#ነቅቻለሁ♥

ነቅቻለሁ ተርፌያለሁ
እራሴን ላድን ቆርጫለሁ
ልኩ ላይ ብርሀኑ ላይ
አይኔ ላፈዝ ጨለማው ላይ
ልፈልገው ከዋለበት
ፍፁም ፍቅር ከሞላበት
እራሱ ላይ ጎዳናው ላይ
ፍቅርን ላገኝ ፊት ለፊት ላይ

መቼ ተሞኘ ብልህ ነው ፍቅር
ክብሩን አይጥልም ከውሸት መንደር
ከቅብዝብዝ ጋር መች ይረጋጋል
አይታለልም ሸንጋዩን ያውቃል

መንገዴ ለየ
አይኔ ብርሀን አየ
መንገዴ ለየ
አይኔ ብርሀን አየ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ሆሆሆ
በቃ በቃ ይዬዬ

ነቅቻለሁ ተርፌያለሁ
እራሴን ላድን ቆርጫለሁ
ልኩ ላይ ብርሀኑ ላይ
አይኔ ላፈዝ ጨለማው ላይ
ልፈልገው ከዋለበት
ፍፁም ፍቅር ከሞላበት
እራሱ ላይ ጎዳናው ላይ
ፍቅርን ላገኝ ፊት ለፊት ላይ

የተራበ ልብ ፍቅርን ይጏጏል
ከውነት ቤት ሄዶ እውነት ያንኯኯል
ደጁን ለዐና እዛው ቆይቶ
የራሱ ያቅፍል በሩ ተከፍቶ
መንገዴ ለየ
አይኔ ብርሀን አየ
መንገዴ ለየ
አይኔ ብርሀን አየ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ድሮ
የጨለማው ኑሮ
በቃ በቃ ሆሆሆ
በቃ በቃ ይዬ

 ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ሰራዊታቸው የዓድዋን የክተት ዘመቻ አዋጅ አውጀው መላው ኢትዮጵያዊ ወደ ዓድዋ ጉዞ የጀመሩበት ቀን ጥቅምት 2 1888 ዓ.ም. ለእኛ ኢትዮጵያዊያን የአንድነት ማሳያች...
02/10/2019



ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እና ሰራዊታቸው የዓድዋን የክተት ዘመቻ አዋጅ አውጀው መላው ኢትዮጵያዊ ወደ ዓድዋ ጉዞ የጀመሩበት ቀን ጥቅምት 2 1888 ዓ.ም. ለእኛ ኢትዮጵያዊያን የአንድነት ማሳያችን፤ የጋራ ታሪካችን ምስክር በመሆኑ፦
"ዓድዋን ያሸነፍነው አንድ ሆነን ስንነሳ ዛሬ ነው!" በሚል መሪ ሀሳብ በየዓመቱ እንደምናከብረው ሁሉ ዘንድሮም ተዘጋጅተናል።
ተዘጋጅተው ይጠብቁን!
በዕለቱም የዘንድሮ ጉዞ ዓድዋ 7 ምዝገባ ይጀመራል።

09/06/2019

†††˚˚ የእንባ ግማድ ˚˚ †††

ጉም ተጠቅልሎ ዳመና ታጥፎ
የነፋስ ካስማ ሰማይ ደግፎ
ኮከብ ደርድሮ ጨረቃ አንጥፎ፣
በፍቅር አምሳል በፀሐይ ውበት
በአፈር ገላዬ
ህይወቴ ቤዛ እንድታፈራ
አምላክ በጥበብ
የውበት ፍሬ ውስጤ ሲዘራ፣
ልቤ ከልቧ አበባ ቀስሞ
የማር አለላ ከንፈሯን ስሞ
የአንገቷ ጠረን
ፀሐይ ውበቷ ሳቋ እያማረኝ፣
በጥቁር ቀለም ደመናው ቀልሞ
ኳክብትን ጋርዶ ጉሙን አግዝፎ
የናፍቆት ምሴን ምጌ ሳልጠግበው
የሰማይ እምብርት እውነት ዘርግፎ
ዙሪያ አንገቴን እንባ አረጠበው፡፡
††† ˚˚˚˚ †††
በምድር ትቢያ ቋጥኙ ገዝፎ
የሰማይ ጽላት መክሊቴን ጽፎ
በሰባራ ገል ዕድሏን ሰፍሮ
የዐይኗን ብሌን ብርጭቆ ሰብሮ
የእንባ ጅረት ቁልቁል ሚወርደው
ሀዘን ነው ደስታ? ምን አበቀለው?
ዝናብ ዘለላው በምሽት ረግፎ
ህይወትን ጥሎ አብሯት ሚያለቅሰው
የእንባዋ ትርጉም
ውስጠ ስሜቷ በምን ገብቶት ነው!!!
ፍቅር ሸኝቶ መውደዱን ልኮ
በድን ገላዬ
የሚራመደው መንገዱን ታኮ
በእንባ ሲሸኘኝ ለህይወት ምርኮ…
የዝናቡ ዶፍ ውርጭ ቀላቅሎ
ልብስ አበስብሶ ገላን ቢያርሰው
መች ይበርደዋል
ልቡ በእንባ ነፍሱ በፍቅር የረጠበ ሰው፡፡
††† ˚˚˚˚ †††
የፍቅር ቅኝት እንዳይወለድ
ስንኝ ሲጨስ ቃል በቃል ሲነድ
በጉንጬ እፍኝ ቃላት ተቋጥሮ
በጥርሴ ችንካር ምላሴ ታጥሮ
የእንባ ጅረት
በአንገቴ ሲሰርግ ውስጤን በርብሮ
ልቤ ሲደለቅ እንደ ከበሮ…
የእንባን ቅኔ
ወርቅ የሚፈቱ ከህብረ ቃሉ
ፍሬ ስንኞች በዓለም ሳይበቅሉ
አንደበት ታስሮ ዝምታ ሲነግስ
ወዴት ይመለስ ???
እንዴት ይመለስ ???
††† ˚˚˚˚ †††
ልቤ ከልቧ አበባ ቀስሞ
የማር አለላ ከንፈሯን ስሞ
ከፀሐይ ውበት ሳቋን ሳይጠግብ፣
በእንባ ፍቺ
እንቅልፌ ጠልቆ ወደ ምዕራብ
በቆፈን ሌሊት
ውበት ስጠማ ናፍቆቷን ስራብ፣
የሰማይ ደጃፍ
ምስኮት ተዘግቶ ዝናብ ሲያባራ
ንጋት ተገልጦ ሰማይ ሲጠራ፣
መዓልት ሌሊት
ሲፈራረቁ ነግተው ሲመሹ
የእንባዋን ፍቺ እሷም ሳትነግረኝ
እኔም ሳይገባኝ
የህይወት ምሥጢር እንቆቅልሹ፣
የእንባ ግማድ ታስሮ ባንገቴ
ፍቅሯን በልቤ
ይዠው ኖራለሁ እንደ እምነቴ፡፡

˝ †ስፋዬ ጉዲሳ፣ ግንቦት ፪፫ ፶፻፱ ”

31/12/2018

"እባካችሁ የሰፈር አውራ ዶሮዎች አትረብሹን"

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የየካቲት 12ቱ – ጥቋቁር ሰማዕታት! (አናብስቱ በተኩላዎቹ ተሰለቀጡ-ወዮ! ወዮ! ወዮ!) ከጥቁሩ ሰማይ ሥር፣ ባፍሪካ ትቢያ ላይ፤በጥቁር ሕዝብ ርስት፣ ባፍሪካ ኮከብ-ጣይ፤በጠራራው ቀትር፣ ባ...
19/02/2018

የየካቲት 12ቱ – ጥቋቁር ሰማዕታት!
(አናብስቱ በተኩላዎቹ ተሰለቀጡ-ወዮ! ወዮ! ወዮ!)
ከጥቁሩ ሰማይ ሥር፣ ባፍሪካ ትቢያ ላይ፤
በጥቁር ሕዝብ ርስት፣ ባፍሪካ ኮከብ-ጣይ፤
በጠራራው ቀትር፣ ባውላላ አደባባይ፤
የጥቁሮች ደም ፈሷል፣ ለቅኝ-ግዛት ሲሳይ፡፡
ለነጭ የዛር ግዳይ፣ ለዘር ምሱ አዋይ!
ፀሐይንም ጋርዷት፣ ጥቁር መጋረጃ፤
ምድርም ተጎናጽፋ፣ ጥቁር ከል-ስጋጃ፤
ጥቁሩ ዓለም ተግቷል፣ ያዘን-መከር ቀንጃ፡፡
(ግጥም፣ በሰ.ተ.ጂ)

የኢትዮጵያና የአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ በሆነችው በአዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ሃውልቶች መካከል፣ አምስቱ በኢትዮጵያና በኢጣሊያን መካከል በ1886ዓ.ም እና በ1928-1933ዓ.ም ለተደረጉት ጦርነቶች የድልና የግፍ መታሰቢያ የታነጹ ናቸው፡፡ አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው “የአዱዋን ድል” የምንዘክርበትና አራት ኪሎ አደባባይ ላይ የቆመው “የሚያዝያ 27ን የነፃነትና የድል በዓል” ለመዘከር የቆሙ ሁለት ሃውልቶች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ ለገሀር የሚገኘው “የይሁዳ አንበሳ” ሃውልት ደግሞ በፋሺስት ኢጣሊያን በ1928ዓ.ም ዘርፎ ተወስዶ የነበረና፣ በጥቅምት 23/1955ዓ.ም እንደገና ተመልሶ የቆመ ነው፡፡ አሁን በባቡር መስመር ግንባታ ሰበብ የተነሳውና በአምስት ኪሎ ብሔራዊ ሙዚየም ውስጥ የቆመው የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልትም አራተኛው ማሳያ ነው፡፡ አምስተኛውና በቁመት ከሁሉም ጠሚበልጠው ደግሞ፣ በ1951ዓ.ም በዩጎዝሎቫያው ፕሬዝዳንት ማርሻል ዴኒስ ቲቶ ልዩ ድጋፍ እንደገና የቆመው የስድስት ኪሎው “የየካቲት 12ቱ ሰማዕታት” መታሰቢያ ሃውልት ነው፡፡ ሁለት የድል ማብሰሪያ ሃውልቶች፣ እና ሦስት የመከራና የእልቂት መዘከሪያ ሃውልቶች ቆመዋል፡፡ (በዛሬው መጣጥፋችንም ስለዚህ ስለአምስተኛው ሃውልትና ሊዘክራቸው ስለቆመው በመቶ ሺዎች ሲለሚቆጠሩት ሰማዕታት ይሆናል፤ መልካም ንባብ እንደሚሆንላችሁ እንመኛለን፡፡)

የካቲት 12 ቀን 1929ዓ.ም የዋለው በዕለተ ዓርብ ነበር፡፡ ሩዶልፎ ግራዚያኒ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ረፋድ 4፡00 ሰዓት ላይ፣(ከቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ መልስ) በገነተ-ልዑል ቤተ መንግሥት ፊት-ለፊት (የዛሬው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6ኪሎ ካምፓስ ፏፏቴው ጋር ነው፤) እንዲሰበሰቡ አዘዘ፡፡ ለነዲያንና ለችግረኞችም ለእያንዳንዳቸው ሁለት-ሁለት ሊሬ እንደሚሰጥ ጭምር አስለፈፈ፡፡ ነገር ግን፣ “ልክ በ4፡00 ሰዓት ይጀምራል” የተባለው ፕሮግራም እስከ 4፡55 ድረስ ሳይጀመር ቀረ፡፡ ሰበቡም የግብፃዊው አቡን፣ (አቡነ ቄርሎስ፣) “ታምሜያለሁ!” ብሎ በመቅረቱ/በመዘግየቱ የተነሳ ነበር፡፡ እስኪመጣም ድረስ የዕለቱ መርሃ-ግበር ለአንድ ሰዓት ያህል ዘገየ፡፡ ወታደሮች ተላኩና አበኑ ልክ 4፡55 ሲሆን ቤተ መንግሥት ደረሰ፡፡ ወንበር መጣለትና ከግራዚያኒ በስተቀኝ በኩል፣ ከከፍተኛዎቹ የፋሺስት ባለስልጣናትም ጎን ተቀመጠ፡፡ ከግራዚያኒም በስተግራ በኩል ጄኔራል ጋሪባልዲ፣ ደጃዝማች ኃይለ ሥላሴ ጉግሳ (የአፄ ዮሐንስ የልጅ-ልጅ)፣ ራስ ኃይሉ(የጎጃሙ ንጉስ ተክለ ሃይማኖት ልጅ) እና ከሌሎች ባንዶችም ጋር ተጎልቶ ነበር፡፡ ልክ 5፡00 ሲል ግራዚያኒ ሻኛው እንዳበጠ ኮርማ ቁና-ቁና እየተነፈሰ ኢትዮጵያውያንን ያበሻቅጥ ጀመር፡፡ “ይኼው አለሁ!… ሞቷል እያላችሁ የምታወሩትና የምታስወሩት ኹሉ ከንቱ ሟርት ነው፡፡” እያለ የኢትዮጵያን ሕዝብ በገዛ አገሩና በገዛ መሬቱ ላይ ያዋርደው ጀመር፡፡ (ግራዚያኒና ተባባሪዎቹ የነበሩበት ቦታ ወደ ራስ መኮንን አዳራሽ መግቢያ በር ላይ ያለው-የቤተ መንግሥቱ በረንዳ ላይ እንደነበር ልብ ይሏል፡፡)

ልክ 5፡15 ሰዓት ገደማ ሲሆን አብራሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም (የተባሉት ሁለት የኤርትራ ክፍለ-ሀገር ተወላጆች) ከበረንዳው በላይ ባለው ፎቅ ላይ/ግራዚያኒ ከቆመበት ሥፍራ ላይ ጥቁር ሸሚዝ (ፋሺስቶች ለባንዶች ያለብሱት የነበረውን ወታደራዊ/የአስካሪስ ልብስ) ለብሰው፣ኩታቸውን ተከናንበው ታዩ፡፡ ዓይኖቻቸው በንቃት ይንተገተጋሉ፡፡ ልክ 5፡30 ሲሆንም ለነዲያን ምጽዋት መሠጠት ተጀመረ፡፡ በሥፍራው ከሦስት ሺህ ሁለት መቶ (3,200) በላይ ነዲያን ተሰብስበው ነበር፡፡ እንዲሁም ግብር-ሊበሉ የመጡ በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ግራዚያኒና ግብረ-አበሮቹ ከቆሙበት ስፍራ በአሥር ወይም አሥራ ሁለት ሜትር ርቀት ላይ ከበው ቆመዋል፡፡ ከሰዎቹም ፈንጠር ብለው ከዘጠና የማያንሱ መትረየሳቸውን የደገኑ ሶላቶዎችና አስካሪዎች በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ነዲያኑን ከበረንዳው አካባቢ ራቅ እንዲሉ ይገፏቸው ጀመር፡፡ ጫጫታና ውካታው ከፍ ብሎም ለአስር ደቂቃዎች ያህል ተሰማ፡፡

ነገር ግን፣ ኢያን ካምፔል (Ian Campbell; “The Plot to Kill Graziani”. ብሎ በ2003ዓ.ም ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ እንደዘገበልን ከሆነ፣) በግምት ከ5፡40 እስከ 5፡45 ድረስ ባሉት አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ተከታትለው ቦንቦች እነአብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ካሉበት ደርብ ላይ ቁልቀል ተወረወሩ፡፡ የመጀመሪያው ቦንብ እንደተመረወረ፣ ብዙዎቹ ታዳሚዎች ለስብሰባው ማድመቂያ መድፍ የተተኮሰ ነበር-የመሰላቸው፡፡ ሁለተኛው ሲወረወር ግን፣ አቡነ ቄርሎስና ግራዚያኒ መሬት ያዙ፡፡ በስተ-ግራ በኩልም ያሉት ሁለት ጥበቃዎች ወዲያውኑ ሞቱ፡፡ ሦስተኛውም ሲወረመር፣ ግራዚያኒ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሊገባ ፊቱን አዙሮ መሸምጠጥ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም፣ የሦስተኛው ቦንብ ፍንጣሪዎች አቆሠሉት፡፡ ዳኒሎ ብቢሪንዴሊ የተባው የካሜራ ባለሙያም እየደማና እያቃሰተ የነበረውን ግራዚያኒን ከወደቀበት አንስቶ፣ ከ5፡50 እስከ 6፡00 ባሉት አስር ደቂቃዎች ውስጥ ወደ መኪናው ከተተው፡፡ በፍጥነት ወደ “ኦስፒዳሌ ኢታሊያኖ” (“የጣሊያ ሆስፒታል” ለማለት ነው፤ የዛሬው “ራስ ደስታ ሆስፒታል” መሆኑን ልብ ይሏል፤) ወሰዱት፡፡

ከየካቲት 12 ቀን 1929ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓትም ጀምሮ እስከ የካቲት 14 ቀን 1929 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ድረስ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በግፍ ተፈጁ፡፡ (የሚነገረው ቁጥር በአዲስ አበባ ብቻ የተፈፀመውን ግድያ የሚያሳይ ብቻ ነው፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገድምና በዝቋላ አቦ የተረሸኑትም መነኮሳትና ምዕመናን እጅግ በርካታ ናቸው፡፡) በ1934ዓ.ም የመጀመሪያው የየካቲት 12ቱ ሰማዕታት መታሰቢያ በዓል በተከበረበት ዕለት የወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ክስተቱን እንዲህ ሲል ነበር የዘገበው፤ “ያቺን ቀን እናስባት፤ አንርሳት፡፡ የኢትዮጵያ ሰማዕታት የክብር አክሊል የተቀበሉባትን፣ ደማቸው እንደጎርፍ በግፍ የፈሰሰባትን፣ ሥጋቸው እንደክትፎ የተከተፈባትን፣ አጥንታቸው እንደገል የተከሰከሰባትን፣ ዕለተ-ዓርብን፣ ያቺን ቀን አንርሳት!…መቼም የዕለተ-ዓርብ መከራና ሃዘን ማለቂያ የለውም! አስቀድሞ፣ ንጹሑ ክርስቶስስ በዕለተ-ዓርብ በ33ዓ.ም አልነበር የተሰቀለው!? የካቲት 12/1929ዓ.ም ደግሞ ሁለተኛው የንጹኃን ደም በከንቱ የፈሰሰበት ዕለት ኾነ፤” እያለ ይቀጥላል፡፡

የዚህም ጊዜ አርበኞቻችን ነቁ፤ ቆፍጠን ብለውም ታጠቁ! የደረሰው ግፍ፣ የተፈፀመው የግፍ-ግፍ አበረታቸው፡፡ የነጭ ፋሺስቶች ግፈኝነት እንደእግር እሳት መላ-አካላታቸውን አንገብግቦት ኖሮ፣ኢትዮጵያ እየበረታች ሄደች፡፡ ጥቁሮቹን አርበኞች፣ በከንቱ የተከነበለው “የጥቋቁሮቹ ሰማዕታት” ደም አጀግኗቸው ኖሮ፣ ከሸዋ እስከ ሽራሮ፣ ከኦሜድላ እስከ ቆራሄ፣ ከሞያሌ እስከ ዠማ፣ ከዱር-ቤቴ እስከ ሚሌ አንጠራወዛቸው፤ አንቀሳቀሳቸው፡፡ “የጥቋቁሮቹ ሰማዕታት” ደም እጅግ ንሮና ግሞ፣ የፋሺስትን ሃይል ይለበልበው ገባ፡፡ ራስ አበበ አረጋይ፣ ራስ መስፍን ስለሺና ወንድማቸው (ሌ/ጄኔራል) ደጃ/ች ይልማ ስለሺ፣ ደጃ/ች አባ ኮራን፣ ፊት/ሪ ገረሱ ዱኪ፣ ፊት/ሪ ገለታ ቆሪቾ፣ ፊት/ሪ በቀለ ወያ፣ ልጅ ጃጋማ ኬሎ፣ ደጃ/ች ፀሐይ እንቄ-ሥላሴ፣ ደጃ/ች ተሾመ እንቄ-ሥላሴ፣ ራስ ስዩም መንገሻና ባለቤታቸው፣ እና ሌሎችም ሆነው ከያሉበት የጣሊያንን ወራሪ ለመመከት ተንቀሳቀሱ፡፡ የሸዋው፣ የወሎው፣ የጎጃሙ፣ የጎንደሩ፣ የትግራዩ፣ የከፋው፣ የጋሞ-ጎፋው፣ የኢሉ-አባቦራው፣ የሲዳሞው፣ የአሩሲው፣ የሲዳሞው፣ የባሌውና የሐረርጌው ባንድነት ሆነው ከገጠር እስከ ከተማ ተንቀሳቀሱ፡፡ አንገዛም አሉ፡፡ የገጠሩና የከተማው ህዝብም ባንድነት ስለተረዳዳም፣ “አለሁ! አለሁ!” ይል የነበረው የፋሺስት ጦር እንደሌለ ሆነ፡፡ ኢምንት ሆነ፡፡ (ሕዝብ ሲተባበርና ሲረዳዳ፣ “አለሁ! አለሁ!” የሚሉ ግፈኞችና ጨቋኞች የሉም፡፡ መረዳዳቱና መተባበሩም በጦርነትና በጭንቅ ሰዓት ብቻም ሳይሆን፣ በአንፃራዊ ሰላምም ወቅት መደገም እንዳለበትም ለማስታወስ እንወዳለን፡፡)

ይህ በእንዲህ ሳለም፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት፣ በፋሺስት ኢጣሊያ ስላለቁት ወገኖቻችንና ስለደም ካሳቸው በተመለከተ ጥያቄ ማቅረብ የጀመረው ከ1936ዓ.ም ወዲህ ነው፡፡ ጥያቄውን የበለጠ ፖለቲካዊና ዓለማቀፋዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ፣ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተቀየረበት የመጀመሪያው ዓመት ላይ፣ (በ1938ዓ.ም) የኢትዮጵያ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ሦስት ጥያቄዎችን አቅርቦ ነበር፡፡ “አንደኛ፣ ለኢጣሊያ ፋሺስታዊ መንግሥት ወረራ መነሻ የሆኑት ጥንታዊ ክፍለ-ሀገሮች ኤርትራና ሱማሊያ፣ ለኢትዮጵያ እንዲመለሱላት፤” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛ፣ “ለተቃጠሉት አብያተ-ክርስቲያናት፣ ለተበረበሩትና ለተዘረፉት ንዋየ-ቅዱሳት፣ ለተደመሰሰው የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብትና ንብረት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ በግፍ ለተሰውት ከ750ሺህ በላይ ንጹኃን ኢትዮጵያውያን ሕይወት፣ የኢጣሊያን መንግሥት ካሳ እንዲከፍል፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ ሦስተኛው ጥያቄ ደግሞ፣ “በኢትዮጵያ ለተፈጸሙት ወንጀሎች ኹሉ ዓብይ አርእስት ሆኖ የሚገመተው በግራዚያኒ መሪነት የተፈፀመው የየካቲት 12/1929ኙ ዓ.ም ዕልቂት፣ ከማናቸውም የፋሺስት የግፍ ሥራዎች ኹሉ ከፍተኝነትና ኢ-ሰብዓዊነት ስላለውም፣ ጭፍጨፋው እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና ግብረ-አበሮቻቸው በሙሉ፣ ፍርዳቸውን ግፉን በሰሩበት ቦታ እንዲቀበሉና ግፉ ስለተፈፀመባቸውም ወገኖቻችን የደም ካሳ እንዲከፈል፤” የሚጠይቅ ነበር፡፡ በኹሉም/በሦስቱም ጥያቄዎች ውስጥ ገኖ የሚታየው ጥያቄ፣ “የጥቁሮቹ ሰማዕታት” ጩኸት ነው፡፡

ሆኖም ግን፣ በሚያዝያ 19/1940ዓ.ም ኢትዮጵያ (ያን ጊዜ፣ በምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በነበሩት-ክቡር አቶ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ አማካይነት) ያቀረበችው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ ነበር፡፡ ይህንም ውሳኔ እንደኔዘርላንድና ኢራን የመሳሰሉት አገሮች በፓርላማዎቻቸው አቅርበው አጸድቀውታልም፡፡ ነገር ግን፣ የኢጣሊያና የሮማንያ መንግሥታት ባቀረቡት ይግባኝ መሠረት፣ (ለመንግሥታቱ ዋና ፀሐፊ ባስገቡት ማመልከቻ መሠረት፣) ጉዳዩ እንደገና እንዲመረምር ተደረገ፡፡ ከዚያንም ጊዜ ጀምሮ፣ እስካለንበት ዘመን ድረስ እንደተዳፈነ ነው፡፡ ይባስም ብሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ “ጭፍጨፋው እንዲፈጸም ትዕዛዝ የሰጡት የጦር አዛዦችና ግብረ-አበሮቻቸው በሞላ የጦር ወንጀሉን በፈጸመበት ቦታ/ሀገር ፍርዳቸውን መቀበል ይገባቸዋል፤” ብሎ ያመለከተውን እግዚኦታ ከቁብም ሳይቆጥሩ፣ ለዚያ የተኩላ ልጅ (የሚላኑ መስፍን) ብለው ሃውልት አቆሙለት፡፡ ይህ አባዜ፣ የነጩ ዓለም ለጥቁሮች ያለውን ከፍተኛ ንቀትና መዘባበት የሚያሳብቅ ነው፡፡ መረሳት የሌለበት ግዙፍ እውነት ከፊታችን ተገትሯል፡፡ እርሱም የያንኪዎቹና የያፌታውያኑ ናላ፣ ለእኛ ለካማውያን ወንድሞቹ ያለውን አሉታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ በተከታዮቹ አንቀፆች አማካይነት ላብራራው እወዳለኹ፡፡

ነጮቹ ያፌታውያን፣ የቀይ ሕንዶቹን ከምድረ-ገጽ ጠራርገው ሲያጠፏቸው ለታሪክና ለህሊና ለመታሰቢያ የሚሆን ሃውልት አላቆሙላቸውም፡፡ ያንን ዘረኛና ኢ-ሰብአዊ ግፍ የፈፀሙትም አረማዊዎች አልተጠየቁም፡፡ ነጮቹ ያፌታውያን፣ ባህር አቋርጠው ሄደው አውስትራሊያ ያሉትን የአቦርጂኒያ ጥቁሮች ሲደመሷቸውም ተመሳሳይ መታሰቢያ አላቆሙላቸውም፡፡ ለመቶ ዓመታት ያህል የአውሮፓ የባህር ላይ ወንበዴዎች (Pirates) እጅግ ቆፍጣናዎቹንና ጡንቸኛዎቹን ወጣቶች እየፈነገሉ ለሸንኮራ አገዳ ቆረጣና ለእረኝነት ሲወስዷቸው የጮኸ የለም፡፡ ያንን ግፍና ኢ-ሰብዓዊ በደልም የሚዘክር በቂ ስነ-ጽሑፍና ኪነጥበባዊ ሥራ አልተሰራላቸውም፡፡ (ታላቁ ዚቀኛ ሼክስፒር እንኳን (The Tempest) በተባለው ተውኔቱ አማካይነት በአፍሪካውያኑ ላይ የተደረገውን የባሪያ ፍንገላ ልዩ እውቅና ሰጥቶታል፡፡) ከኩሽ ቤት/ከሊቢያና ከሞሮኮ የሄዱት ኩርዶች፣ ቫስኮችና ጂብሲዎችም በአውሮፓና በመካከለኛው ምስራቅ አገር-አልባ ሆነው፣ ከሰብዓዊ ፍጡር በታች ተደርገው ሲኖሩ ማንም ከመጤፍ አልቆጠራቸውም፡፡ ማንም ታሪካዊ መሬታቸውንና ግዛታቸውን አልመለሰላቸውም፡፡ ደቡብ አፍሪካ-ሱዎቶ ላይ በጠራራ ፀሐይ የተጨፈጨፉትን ጥቁር አፍሪካውያን የሚዘክር አንድም እንኳን ፊልም አልተሰራላቸውም፡፡ ሃውልትም አልቆመላቸውም፡፡ ነገር ግን፣ በ1983ዓ.ም በጥቁር ወንድማማቾች መካከል የተደረገውን የሩዋንዳና የቡሩንዲውን (የሁቱና ቱትሲ) ሰብዓዊ ዕልቂት፣ አንዴ “የዘር ማጥፋት! Genocide” ሌላም ጊዜ የዘር ማጥራት! Ethnic Cleansing” ወዘተርፈ የሚል ቅጽል ስም እየሰጡ፣ በሆሊውድና በሌሎችም ተቋሞቻቸው አማካይነት ይሸቅሉበታል፡፡ መጽሐፍ ጽፈውም ይቸበችቡታል፡፡ ሩዋንዳውን የቡሩንዲውን፣ የአንጎላውን፣ የዛየር ኮንጎውን፣ የላይቤሪያውን፣ የሱማሌያውን፣ የሱዳኑንና የዚምባቡዌውን ችግር ከመጠን በላይ እያጋነኑ በማቅረብ ለካም ቤት ያላቸውን ንቀትና ፌዝ ይግቱናል፡፡

ነገር ግን፣ የቦሲኒያውና የሄርዞ-ጎቪኒያው ጉዳይ ሲመጣ ሌላ ሽፋን ይሰጡታል፡፡ የሃይማኖት መለያየት የፈጠረው ጣጣ እንደሆነ ሊሰብኩን ይጣጣራሉ፡፡ አለያም ደግሞ የርዕዮተ-ዓለም ግጭቶች ጣጣ ውጤት እንደተፈጠረ አድርገው ሊያሳምኑን ይፍጨረጨራሉ፡፡ ይህ ዘረኛና ከያፌታዊ ትምክህት የመነጨው አስተሳሰብ ነው፤ በተለያየ ዘመን በከንቱ የተሰውትን ጥቋቁር ሰማዕታት ደመ-ከልብ ያደረጋቸው፡፡ በየትም ቦታ ጥቁሮች ለያፌታውያንና ለአንዳንድ ቡርዣ ሴማውያን አሽከርና አገልጋይ ሆነው የምጽዓት ጊዜ እንዲደርስ ይፈለጋል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችልበት መጠነኛ እድልም አለው፡፡ የካም ቤት ተከፋፍሎና ተበታትኖ ነው ያለው፡፡ ታላቁ ንጉሠ ነገሥታችን አፄ ኃይለ ሥላሴና እነአቶ ከተማ ይፍሩ የተለሙትን አፍሪካንና መላውን የጥቁር ህዝብ አስተባብረን እንዲረዳዳ ማድረግ ካልቻልን ያፌታውያኑ እንደልባቸው ይፈነጩብናል፡፡ አንዳንድ ሴማዊ ቡርዣዎችም፣ እንደባሪያ ፈንጋይ እየሆኑ፣ ሴቶቻችንን ለጭን-ገረድነት፣ ወንዶቻችንንም ለዘበኝነት ይዳርጓቸዋል፡፡ (እንዳጋጣሚ ሆኖ፣ በአሜሪካንም-ይህ ወር የጥቁሮች ወር ነው፡፡ በአፍሪካ ደግሞ ትልቁ የጥቁር ህዝብ ድል የተበሰረበት የአዱዋም ድል የሚከበረው በዚሁ ወር ነው፡፡ በተጨማሪም ትልቁ የጥቁር ሕዝቦች ኢ-ሰብዓዊ ጭፍጨፋም የተካሄደበት ወር ነው፡፡ በመሆኑም፣ በመላው ዓለም ያሉትን ጥቁሮች፣ በከንቱ ስለቀሩት “ጥቋቁር ሰማዕታት” ጋራ ልንጮኽላቸው ይገባናል፡፡)

ማጠቃለያ፤
በሀገራችን የኖረ አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው፣ “በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል፤ ወይም እኩል ነው፤” ይባላል፡፡ የባርነትን ዋጋ ባንቀምሰው ኖሮ፣ የነፃነትን ዋጋና ጣዕምም አናውቀውም ነበር፡፡ በነፃነት ደጃፍ መኖርን የለመደ ሰው፣ ከባርነት ይልቅ ሞትን ይመርጣል፡፡ ለኢትዮጵያውያንንና ለመላው የአፍሪካ ጥቁር ህዝቦች የባርነትን ብርቱ ስቃይ ከሚያሳዩት ቀኖችም አንዱ “የየካቲት 12ቱ የጥቋቁር ሰማዕታት”በዓል ነው፡፡ ከሰባ ስምንት ዓመታት በፊት በጥቁር አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመው ግፍ ያዩት ሰዎች እጅግ ነው የሚያንገፈግፋቸው፡፡ የብሔራዊ ነፃነታችን ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን በኢትዮጵያና በአፍሪካ አኅጉር መናገሻ ከተማ በማይውለበለብብት በዚያ የባርነት ወቅት፣ በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ እንኳን ከሰላሳ ሺህ በላይ ዜጎች አልቀዋል፡፡ ሰንደቅ ዓላማችን በግፍ ወርዶ የፋሺስት ባንዲራ ከተካው አስር ወር እንኳን ሳይሞላው፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ኃዘን ሰፍኖ ነበር፡፡ ህዝቡ አቀርቅሮ መሄድ ጀምሯል፡፡ ኩራት የለም! እራትም አልነበረም፡፡ አለኝታ የለም፤ ገበያና አደባባይም ወጥቶ በሰላም ለመመለስ ዋስትና አልነበረም፡፡
የጥቁር ህዝብ የድል-ብስራት ማወጃ የሆነችው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በባርነት ሥር ሆነው እጅግ ተሳቀዋል፡፡ በባርነት ስር ያለ ህዝብ ማናቸውም ነገር ሊደርስበት ይችላል፡፡ ቢታሰር፣ ቢረገጥ፣ በሰደብ፣ ቢደበደብም ሆነ ቢገደል ለምን ብሎ መጠየቅ አይችልም፡፡ ምክንያቱም፣ በባርነት ቀንበር ሥር ያለ ህዝብ ማናቸውም መዓት ይደርስበታላ! በባርነት ሥር ያለ ህልውና በእርግጥ ምንም ትርጉም የለውም፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በነፃነት መኖር ሕይወታችን ነው፡፡ ኑሯችን ነው፡፡ በነፃነት መሥራት፣ በነፃነት ማሰብ፣ በነፃነት መማርና በነፃነት መብትን የማስከበር ልዩ ትዕምርት አለን፡፡ ልዩ ባሕልም አለን፡፡ እነዚህ ከሌሉ ሕይወታችን የለችም፡፡ “ያለነፃነት የምንኖር ከሆንን፣ እንደሮቦት የምንንቀሳቀስ ሕቁራን (Inferior) ፍጡሮች ነን፤” ማለት ነው፡፡ ከዚህ ሕቁርነት ሰውሮን፣ የጥቁሮቹን ሰማዕታት ደም ሕያው ለማድረግ ያብቃን!….
( በአዲስጉዳይ መጽሔት፣ በቅጽ 8 ቁጥር 203፣ ቅዳሜ የካቲት 8፣ 2006 ዓ.ም ዕትም ላይ የወጣ ነው፡፡
(በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913056136

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኔታ ኪነ-ጥበባት እና ፕሮሞሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የኔታ ኪነ-ጥበባት እና ፕሮሞሽን:

Share