20/09/2025
ለወደብ ኪራይ የወጣው ከ12 በላይ ህዳሴ ግድቦችን ማስገንባት ይችል ነበር ተብሏል።
📌በዘርፉ በርካታ ምርምሮችን የሠሩት የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ተመራማሪ አቶ ሰለሞን ተፈራ ለጋዜጣ ፕላስ ዘጋቢ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ ላለፉት 36 ዓመታት ለወደብ ኪራይ ለጅቡቲ ያወጣችው ከ12 በላይ የህዳቤ ግድቦችን ይሰራ ነበር ብለዋል።አቶ ሰለሞን እንዳሉት:-
📌ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር ትከፍላለች፤
📌ባለፉት 36 ዓመታትም ለጅቡቲ 72 ቢሊዮን ዶላር ከፍላለች ብለዋል፡፡
📌ይህም ህዳሴ ግድብን ለመገንባትከወጣው ወጪ አንጻር ሲታይ ሀገሪቱ ባለፉት 36 ዓመታት ለወደብ ኪራይ ያወጣችው ዶላር ቢሰላ ከ12 በላይ ህዳሴ ግድቦችን ማሰራት የሚያስችል ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
📌ኢትዮጵያ ለወደብ ኪራይ የከፈለችው 72 ቢሊዮን ዶላር ሀገር ውስጥ ኢንቨስት ቢደረግ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ይበልጥ ያረጋግጥ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡