
23/08/2024
ይህቺ ህፃን አሜን ጥላሁን የምትባል የ2 ወር ጨቅላ ስትሆን ፥ በገጠማት ህመም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ታይታ የዳውን ሲንድረም ተጠቂ መሆኗና የልብ ክፍተት ያለባት መሆኑ ተረጋግጦ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያስፈልጋት፣ ህክምናውም እዚያ የሌለ በመሆኑ ከተቻለ ወደ ውጭ ሀገር እንድትወሰድ ተነግሯቸዋል።
ወላጆቿ ውጭ ሀገር ለመውሰድ የሚያስችል አቅም ስለሌላቸው በአገር ውስጥ የግል ሆስፒታሎች ሲመላለሱ ሰንብተው ህክምናውን እዚሁ ለመስራት የሚቻል መሆኑን ያረጋገጠላቸው ሆስፒታል ቀዶ ህክምናው ከ3-6 ወራት ባለ ጊዜ የግድ መደረግ እንዳለበት እና ወጪውም እስከ 1,600,000 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) እንደሚያስወጣ ገልጠውላቸዋል።
ወላጆቿ ይህንን ወጪ መሸፈን የሚያስችል አቅም ስለሌላቸው ፥ ደጉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ መከራ አውጡን ሲሉ ይማጠናሉ።
እባካችሁ አቅማችሁ የፈቀደውን ሁሉ ታበረክቱ ዘንድ የእናቷን የባንክ ሂሳብ እነሆ በማለት እንለምናለን።
የሂሳቡ ባለቤት :-አየለች ደገፋ ጉርሙ
የባንክ ሂሳብ ቁጥር -
1000281548054 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
ስልክ ቁጥር-0912290503/0913896333